በወታደራዊ አስተዳደር ቀኝ ግዛት ስር የወደቀችዉ ሐገራችን ኢትዮጵያ ብሄራዊ ደህንነቷ በመሽመድመድ ላይ ይገኛል ተባለ

 
መረጃ 03/05/2009 ወታደራዊ ደህንነቱ እና ብሔራዊ መረጃዉ ! በወታደራዊ አስተዳደር ቀኝ ግዛት ስር የወደቀችዉ ሐገራችን ኢትዮጵያ ብሄራዊ ደህንነቷ በመሽመድመድ ላይ ይገኛል። ለዚህ ዉድቀት ከፍተኛዉን ሚና እየተጫወቱ የሚገኙት ወታደራዊ ደህንነቱና ብሔራዊ መረጃዉ የእርስ በእርስ ሽኩቻ ተጠቃሽነቱን ይይዛል። በጌታቸዉ አሰፋ የበላይነት የሚመራዉ ብሔራዊ መረጃ ላለፉት 25 አመታት በአጠቃላይ ሐገራዊ ምስጢር ጉዳዬች ላይ ይሰራ የነበረ ከመሆኑ ባሻገር በሐገር መከላከያ ሰራዊት ዉስጥ ድንበር ዘለል እና ድንበር ገብ ተሻጋሪ መረጃዎችን በመሰብሰብና እንደየ አስፈላጊነቱ ወደ ታች በማዉረድ የወታደራዊ ደህንነቱ የጀርባ አጥንት ነበር :: የህወሃት አተዳደር ለአመታት በደረሰበት ህዝባዊ ተቃዉሞና አመጽ ምክንያት ተሽመድምዶ ሲወድቅ ኮማንድ ፖስቱ የሐገሪቷን ደህንነት በወታደራዊ ቀኝ ግዛት ቁጥጥሩ ስር አስገባዉ። በሐገር መከላከያ ሚኒስቴር ጄኔራል ሳሞራ ዩኑስ መዳፍ ዉስጥ የገባዉን የሐገሪቷ እጣ ፈንታ በኮማንድ ፖስት አማካኝነት ከላይ የወረደላቸውን ትእዛዛት እንዲያስፈጽሙ በሐገር መከላከያ ሚኒስቴርነት የተሰየሙት ጄኔራል ሲራጅ ፈጌሳ ከወታደራዊ ደህንነቱ ዋና መምሪያ ሐላፊ ሜጀር ጄኔራል ገብሬ አድሀነ ( ዲላ ) እንዲሁም ከሜጀር ጄኔራል ሃሺም ኢብራሂም፣ ከሜጀር ጄኔራል መሃሪ ዘዉዴ፣ ከብርጋዴል ጄኔራል አትክልቲ በርሄ፣ ከብርጋዴል ጄኔራል አብርሃ ተስፋዬ፣ ከብርጋዴል ጄኔራል አስካለ ብርሃኔ፣ ጋር በማበር እቅዶችን ማዉጣት ጀመ። በዚህ ወቅት የኮማንድ ፖስቱ አካል ሆኖ ህብረት ዉስጥ መግባት የነበረበት በሐገር ዉስጥ እና ከሐገር ዉጭ በከፍተኛ ሁናቴ የስለላ መረቡን የዘረጋዉ የብሄራዊ መረጃዉ የበላይ ጠባቂ ጌታቸዉ አሰፋ እና በዉስጡ የተካተቱ ከፍተኛ ህዝባዊ ንብረት ፈሶባቸዉ በደህንነት ዙሪያ የሰለጠኑ አባልቶች ለወታደራዊ ደህንነቱ ኮማንድ ፖስት እርሱም ለሜ/ጄ ገብሬ ዲላ አለን የሚሉትን መረጃዎች ሁሉ በመስጠት የእርምጃ አካሄዱና የስልጣን ተዋረዱ ከጌታቸዉ እሰፋ ብሔራዊ መረጃዉ ወደ ወታደራዊ ደህንነቱ እንዲዛወር ስልት ተቀየሰ:: መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ/ም የሚኒስትሮች ምክር ቤት አንቀጽ 13/2 እና በደንቡ እንቀጽ 4 መሰረት መመሪያ አወጥቶ ወደ ተግባር ተገባ ወይም( ህዝብን ወደ ማፈንና መግደል )ተገባ .. የህወሃቱ ኮማንድ ፖስት ገና መስመሩን ከመያዙ ሚስጥራዊ በሆነዉ የኮማንድ ፖስቱ ስብሰባ ላይ ላለፉት 25 አመታት የሐገሪቷን ብሄራዊ ደህንነት ባለማስጠበቅ ለደረሰዉ መንግስታዊ ዉድቀት የጌታቸዉ አሰፋን ብሔራዊ መረጃ መዉቀስ ጀመረ ይህዉም…. 1. ብሔራዊ መረጃዉ እንደሰንሰለት አጠላልፎ የዘረጋቸዉ አባላቱ ሚስጥራዊ መረጃዎችን ያባክናሉ 2. ህዝብ ሊቀሰቅሱና ከፍተኛ ተቃዉሞ ሊያስነሱ የሚችሉ አካላቶች ላይ የተወሰደዉ እርምጃ ያልተጠና ወይም ሆን ተብሎ የተደረገ ነዉ 2…..ሀ. በመረጃዉ ክፍል የተጠለፉ ግለሰቦች ህዝብ ሊቀሰቅሱ እንደሚችሉ እየታወቀ መታፈናቸዉ 2…..ለ. በመረጃዉ ክፍል የተጠለፉ ግለሰቦች ህዝብ ሊቀሰቅሱ እንደሚችሉ እየታወቀ መለቀቃቸው 2…..ሐ. በብሄራዊ መረጃዉ የተጠለፉ ግለሰቦች ከፍተኛ ምርመራ ( ቶርች ) ከተፈጸመባቸዉ በኋላ መወገድ ሲገባቸዉ ወደ ህዝብ መለቀቃቸዉ 3. በመሐበራዊ መገናኛ ዘርፎች ላይ ብሔራዊ መረጃዉ ያሳየዉ ቸልተኝነት 4. በተለይም አላማ ጥራት ያለዉ መረጃ ባለማቅረብ እና አስተማማኝ የደህንነት እገልግሎት ላይ የተፈተኑ ተግባራትን ባለመፈጸም 5. የተሳሳቱና ከእዉነት የራቁ በምስል እና በተለያየ መንገድ የተደገፉ መረጃዎችን በታመኑ የስርዓቱ የመገናኛ አዉታሮች ላይ በድግምግሞሽ እንዲሰራጩ የተደረገበት ምክንያት የብሄራዊ መረጃዉ ጥናትን ተገን ተደርጎ በመሆኑ :: 6. በዉጭ ሐገር የተዘረጋዉ የብሄራዊ መረጃዉ የማግባባትና የእርምጃ አወሳሰድ ስልቶች ግድፈት የተሞላቸዉ እና ዘገምተኛ በመሆናቸዉ፤፤ የሚል ሲሆን….. ኮማንድ ፖስቱ በበኩሉ ወታደራዊ ደህንነቱን በማጠናከር ኮማንድ ፖስቱን ለማራመድ የጌታቸዉ አሰፋ ብሔራዊ መረጃ ላይ ጫና ማሳደር ጀመረ:: የኮማንድ ፖስቱ ስልታዊ አካሄድ የተገለጸለት ብሔራዊ መረጃዉ የብሔራዊ መረጃዉን የደህንነት ጉዳይ አማካሪ ሚኒስቴር ጸጋዬ በርሄ አደራን በመዳፉ በመጨበጥ ላለፉት 25 እመታት በቁጥጥሩ ዉስጥ የነበረዉን የሐገሪቱን የደህንነት ሙሉ ሚስጥር ለኮማድ ፖስቱ የመረጃ ክንፍ ላለመስጠት ነገር ግን ወታደረዊ መረጃዎችን እና ህዝባዊ አመጽን በማኮላሸት ዙሪያ ያሉትን ፍንጮች ብቻ በማቀበል የስቸኳይ ግዜ እዋጁ አካል በመሆን ተከሰተ: በዚህ የዉስጥ መወነጃጀልና መጠላለፍ አደጋ ላይ የሚገኘዉን የሐገራቷን ብሄራዊ ደህንነት ለማከም ይቻል ዘንድ በመሯሯጥ ላይ የሚገኘዉ ኮማንድ ፖስት ተብዬዉ የሳሞራ የኑስ ህወሃትን አድን ሐይል በጅጅጋ ባደረገዉ ሚስጥራዊ ስብሰባ ላይ ያሉትን ሐግራዊ መረጃዎች ባጠቃላይ ሰብስቦ ውደ ሰሜኑ ክፍል እንዲያተኩር የተሰመረበት ሲሆን የብሄራዊ መረጃዉ የስለለላ እባሎችን በወታደራዊ ደህንነቱ የመተካት ስራ በሚስጥራዊ መንገድ እንዲተገበር ተወስኗል:: ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! ( ጉድሽ ወያኔ )
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: