ህወሀት የባንክ ባለአክሲዮኖችን የሚያስደነግጥ ህግ አወጣ

ብሄራዊ ባንክ የግል ንግድ ባንኮች የሌላ ሐገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን የገዟቸውን ሼሮች ባንኮቹ ቀድሞ በነበረው ዋጋ እንዲገዙ፣ መልሰውም አሁን ባለው ዋጋ ለሌሎች እንዲሸጡና ልዩነቱም ወደ ብሔራዊ ባንክ እንዲገባ እንዲደረግ መመርያ መውጣቱን ሰማን፡፡ ለምሳሌ አንድ ባንክ የዛሬ 15 ዓመት ሲቋቋም የአንድ ሼር ዋጋ 500 ብር ቢሆንና 10 ሼር ብትገዛ የዛሬ 15 ዐመት የከፈልከውን 5000 ብር ዛሬ እንዲመለስልህና 10ሩ ሼሮች ደግሞ አሁን ባለው ዋጋ ተመልሰው እንዲሸጡ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ኪሳራ የሌለውና እጅግ አትራፊው የስራ መስክ ውሐ ማሸግና ባንክ ማቋቋም ነው ይባላል፡፡ አንተ የዛሬ 15 ዐመት ኢንቨስት ያደረከው 5 ሺህ ብር ዛሬ ባንኩን የትና የት አድርሶታል፣፤ የኢትዮጵያ የብር ምጣኔ ተመን ሁለት ሶስት ጊዜ ተከልሷል፤ ለዐመታት የቀጠለ ሐገራዊ ባለሁለት አሃዝ የዋጋ ግሽበት አለ፤ ተፈጥሮኣዊ የገንዘብ የጊዜ ዋጋ (Time value of money) አለ የነገሮች የዋጋ ግሽበት አለ፤ የአንድ ሼር ዋጋም 10ና 20 ዕጥፍ አድጓል፤ አንተን ግን ከ15 ዐመት በኃላ ያቺኑ የድሮዋ 5 ሺህ ብር ትመለስልሐለች፤ ያንተን ሼር ደግሞ በ10፣ በ20 ዕጥፍ ዋጋ ይሸጣል፤ ልዩነቱ ደግሞ ብሄራዊ ባንክ ይወስደዋል፡፡ ለሰሚው ግራ ነው፡፡

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: