በፅናት የሚታገሉትን አርበኞች የሚያስቆማቸው የለም፤የድል ፍጻሜ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ነን።

ትግል ሲጀመር ከፍተኛ መስዋትነት እንደሚያስፈልገው ታስቦበት እና ታቅዶበት በከፍተኛ ዝግጅት ነው። ለዚህ ከፍተኛ የአቅም የሞራል እንዲሁም የእስትራቴጂካዊ ስልቶችን ተነድፈውና ታንጸው ውድ እውነተኛ ትግል የገነባን ሃይል ውድ የተባለውን ህይወቱን ሳይቀር ለሚወዱት አገርና ህዝብ ለመሰዋት ቆርጠው በመነሳት ብዙ ተጉዘው የነጻነት ፋና ሊበራ ሲል የድል ብስራት ሊበሰር ሲል አርበኞች ግንቦት ሰባት ላይ በሚደረጉ አጓጉል የስም ማጠልሸት ዘመቻዎች ትግሉን ወደ ኋላ እንጎትተዋለን አልያም አቅጣጫ እናስቀይራለን ብሎ ማሰብ ከሞኝነት የመነጨ ከብስለት ያልመጣ ጊዚያዊ መፍጨርጨር እንጂ ሌላ አይደለም።
ጥቂት የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ጽናትና ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት ለማጎናጸፍ የከፈሉትን መሰዋት 1 ሁለት ታጋዮችን ልጥቀስ። ይሄ ማለት ግን አርበኞች ግንቦት ሰባትን ተቀላቅለው በርሃ በመውረድ ታሪክ ሰርታው ያለፉትን፤ አሁን ላይ ታሪክ እየሰሩ ያሉትን፤ በማስብ እንዲሁም በውጭም ሆነ በአገር ውስጥ ሆነው በተለያዩ መስኮች ደጋፍና ለትግሉ አጋርነታቸውን በመግለጽ የወያኔን እንቅስቃሴ በመከታተል መረጃ ከመስጠት አልፎ መፈናፈኛ የሚያሳጧቸውንም ውድ የኢትዪጵያ ልጆች ታስቦ የተጻፈ ነው።
ወያኔ እንደ ግንቦት ሰባት የሚፈራውም ሆነ የሚያቃዥው ሃይል በኢትዮጵያ ወስጥ የለም። የኢሳትን ሚዲያ የአርበኛች ግንቦት ሰባት ሚዲያ የኢትዮጵያን ህዝብ እስር ቤት ሲያጉር ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አለህ እያለ ነው፡ ይሄ የሚያሳየው ወያኔ በነዚህ የነጻነት ታጋዮች ምን ያህል እንደተሸበረ ነው።
ወያኔ ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌን በመያዙ እንደ ታላቅ ድል በመቁጠር ትግሉ አበቃለት፤ ከእንግዲህ በሃላ የአርበኞች ግንቦት ሰባትን የትግል መረጃ በእጃችን ገብቷል፧ በማለት ሲያደነቁሩን ከረሙ እውነት የሆነው እንደዛ ነውን? የወያኔ አስተሳሰብ እንዳርጋቸውን በመያዛቸው የትግሉን ሚስጢር አገኙትን? ትግሉስ ከአንዳርጋቸው መያዝ በሃላ ወደሃላ ብሏልን? በጥቂቱ እንየው
ከአንዳርጋቸው ጽጌ ቤተሰብ ብንጀምር ቤተሰቡን ጨምሮ ሚሊዮኖች ሰለ አንድዬ ጮኀዋል ድምጻቸውን አስተጋብተዋል። የጀመርከውን ትግል ዳር ሳናደርስ አንመለስም በማለት ወደ ከፍተኛ ትግል ውስጥ ገብተዋል ። ለዚህ በተለያዩ መድረኮች ላይ የአንዳርጋቸው ባለቤትና እንዲሁም እህቱ አንድዬ በመያዙ በተለያዩ መድረኮች ላይ ቁጭታቸውን በመናገር ስናደምጣቸው እንደነበር ሁሉ እስከመጨረሻው በአላማቸው በመጽናት የተጀመረው ትግል በመቀላቀል ወደበለጠ እልህ ገቡ እንጂ ወደ ኋላ አላሉም።
አንዳርጋቸው ጽጌ ሲያዝ ትግሉ አበቃለት ተብሎ በጠባቦቹ ወያኔዎች ልቦና ውስጥ ቢታሰብም ቅሉ ብዙ የሚባሉት በአመራር ላይ ያሉት የገዛ ትልልቅ ስራቸውን የቤተሰቦቻቸውን ጉዳይ ትተው አንድዬን ያሰረውን የወንበዴዎች ስርአት ከስሩ ፈንቅሎ ለመጣል ወደ በርሃ በመውረድ የበለጠ ትግሉ እንዲቀጣጠልና የወያኔን መቃብር ወደማፋጠኑ ስራ የተገባው እንጂ ፈርቶ ወደኋላ የተመለሰም የሚመለስም አንድም ኢትዮጵያዊ ታጋይ የለም።
ለዚህም ነው ትግሉ የመረረ እና የወያኔ ጉጅሌ ከኢትዮጵያ ምድር ጠራርጎ ካላጠፋ እንደማይመለስ ሲያውቁ ጭንቀት ውስጥ በመግባት በተለያዩ ሚዲያዎች እንዲሁም ፌስ ቡክ ላይ የራሱን ጉጅሌዎች በማሰማራት አርበኞች ግንቦት ሰባት ላይ የስም ማጠፋት ዘመቻ የከፈቱት። ወያኔዎች ግራ ሲገባቸው እና መያዥያው መጨበጫው ሲጠፋቸው ከተያዙ በኋላ መፈራገጥ ለመመላለጥ በሚያስብል መልኩ እርግጫቸውን ያበዙት ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሙሉ የወያኔን ስርአትን መቶ በመቶ ስለማይደግፍና ለነጻነቱ ለመብቱ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር እንደሚሰለፍ ሰላወቁት እየሆነም ያለው እውነት ይሄ እንደሆነ ሰለተረዱት የመጨረሻ መፍጨረጨራቸውን ስም በማጥፋት ቢሰማሩም ታጋዮቻችን ወደኋላ ሊመልስ ደጋፊዎችን ግር ሊያስብል የሚችል ምንም ነገር የለም። ስራዎች በአገባቡ እየተሰሩ ስለሆነ።
ወያኔ ባላት መረጃ መሰረት የግንቦት ሰባት ሃይል ከታች እስከ ላይ ድረስ መረቡን የዘረጋ ከተራው ህዝብ እስከ ባለስልጣን ድረስ ስለላውን የተጠናከረ እንደሆነ ሰለተረዱት ምኑን ከምኑ አገናኝተው መመለስ እንደሚችሉ መላው ስለጠፋቸው በወሬ ጠንካራ እንደሆኑ ለመግለጽ ቢሞክሩም የውስጣቸው ባዶነትን ሊሸፍኑበት የሚችል እውቀት ወይም እውነት ሰለሌላቸው ሁሉን ነገር አግጥጦ ወደመጨረሻው ምዕራፍ መምጣቱ ያስጨነቃቸው ወያኔዎች ከመጣባቸው አደጋ ለማምለጥ የኢንተርኔት ታጋዮችን በመመልመል እየተፍጨረጨሩ የሚገኙት።
ያም ሆነ ይህ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያውቀው የሚገባው ህውሃት ባሰማራቸው ስም አጥፊዎች ትግሉን ወደኋላ እንመልስዋለን ብለው የሚያስቡት ቅጥረኞችን ወደፊት የኢትዮጵያ ህዝብ ቅጣቱን ስለሚሰጣቸው እነሱን ትተን ትግሉ የሚጠይቀውን ስራ በመስራት የድላችንን ብስራት ለማክበር በቆራጥነት የሚታገሉትን ታጋዮች ሊያስቆማቸው የሚችል ምንም ሃይል እንደሌለ በመገንዘብ የድል ፍጻሜ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንዳለን ለማስገንዘብ እወዳለው።
ላይጨርሱት የተጀመረ ትግል የለም፡፡
ድል ለአርበኞች ግንቦት ሰባት!!
ሞት ለጨቋኞች ለገዳዮች!!
ሳሙኤል አሊ

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: