በአየር ሃይል አብራሪዎችና ቴክኒሻኖች ላይ እርምጃ መወሰድ ተጀመረ

በኦሮሚያና በአማራ ከልል የተነሳዉን ህዝባዊ ተቃዉሞ ተከትሎ በኢትዮጵያ አየር ሀይል አባራሪዎችና ቴክኒሻኖች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነዉ።
ገዢዉ ፓርቲ በኢትዮያ አየር ሀይል ዉስጥ በሚገኙ የተለያዩ ምድቦች ዉስጥ ባካሄደዉ ግምገማ ከተቃዉሞዉ ጋር በተያያዘ ግንኙነት አላቸው ተብሎ በሚጠረጠሩ አባላት ላይ ከእስር እስከ ስራ ማገድ እርምጃ እየወሰደ ነው።
በምስራቅ አየር ምድብ በተዋጊ ሄሊኮፕተር በረዳት አብራሪነት ተመድቦ የሚገኘዉ መቶ አለቃ ገመቹ ሀሰን ከግምገማ በሁዋላ ከአብራሪነት የታገደ ሲሆን፣ የግምገማው መሪ የነበረዉ የአየር ሃይል ም/ል አዛዥና የዘመቻ ሃላፊ የሆነው ብ/ጄኔራል መአሾ ሃጎስ ስሙን በመጥራት “ በረራ እንድታቆም የተደረገበትን ምክንያት ታዉቃለክ?” ብሎ ሲጠይቀዉ ፣ መቶ አለቃ ገመቹም በንዴት “ አዎ የታገድኩበት ምክንያት ገመቹ ሰልሆንኩነዉ” ብሎ መልስ ሰጥቷል። ይህን ተከትሎ አብራሪው በአሁኑ ሰአት ሙሉ በሙሉ ከስራው ታግዶ ይገኛል።
በሌላ በኩል በምዕራብ አየር ምድብ በተደረገዉ ግምገማ የሚግ 23 ጀት አብራሪ የሆነው መ/አ መስራች እንዳለ በአማራ ክልል እየተካሄደ ካለው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር ግንኙነት አለህ በማለት እርምጃ ሊወሰድበት እንደሆነ ከአየር ሃይል የአየር ሃይል ምንጮች ገልጸዋል። መ/አ መስራች እንዳለ ላይ ስለሚወሰድበት እርምጃ ከፍተኛ የአየር ሃይሎ አዛዦች እየመከሩ የሚገኝ ሲሆን እስካሁን ባገኘነው መረጃ መሰረት ውሳኔ እንዳልተሰጠበት ታውቋል።
ከዚህ በፊት ከማእከላዊ አየር ምድብ ተይዘዉ የታሰሩት 3 አብራሪዎች ከ2 አመት በላይ ተፈርዶባቸዉ ናዘሬት እስርቤት ይገኛሉ። በማዕከላዊ አየር ምድብ በተደረገ ግምገማ ላይ የአየር ሃይል አባላት ስለታሰሩት አብራሪዎች በማንሳት “እነሱ ያለጥፋታቸዉ ነዉ የታሰሩት፤ አየር ሃይሉ ያለምንም ምክንያት ሰዎችን እያሰረና እያባረረ ተቋሙን እየጎዳ ነዉ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ አመራሮቹ ማስተካከል አለባቸዉ” በማለት አባላቱ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በአየር ሀይል አብራሪዎችና በስርአቱ ከፍተኛ የጦር አዛዦች መካከል ከፍተኛ የሆነ አለመግባባት እንዳለ ከአየር ሃይል ያሉ ምንጮቻችን ገልጸዋል። የአየር ሃይል አብራሪዎች ባለው የስራ ብልሹነት ምክንያት ስራዎች እየተስተጓጎሉ ነው በማለት ቅሬታቸውን ይገልጻሉ። ለስርአቱ ታማኝ ደጋፊዎች የሚባሉት አብራሪዎች ጥፋት ቢሰሩም እንኳን ተጠያቂዎች አይደረጉም።
በምስራቅ አየር ምድብ ማዘዣ በሆነው ድሬዳዋ አየር ሃይል ሶሰት ሄሊኮፕተሮችን በመግጨት ከባድ ኪሳራ በተቋሙ ላይ ያደረሰዉ ሌ/ኮ ፀጋ ዝአብ ካሳ የተባለ የሄሊኮፍተር አብራሪ በአሁኑ ሰአት ምንም እርምጃ ሳይወሰድበት በስራው ላይ ይገኛል። ተቋሙ እንደዚህ እይነት ከባድ ኪሳራ ባደረሱት አካላት ላይ እርምጃ ሳይወስድ በሌሎች አብራሪዎች ላይ አላግባብ የሚወሰዱ እርምጃዎች በአየር ሃይል አባላት ላይ ከፍተኛ የሆነ ቅሬታን እያስነሳ ነው።
ለአገዛዙ ታማኝ አይደሉም ተብለው በሚጠረጠሩ የአየር ሃይል አብራሪዎች ላይም ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑን ምንጮቻችን ገልጸዋል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: