ይኽ ትግል ዳር ሳይደርስ ወደ ኋላ አይመለስም!

14012564_10205198112430990_355381106_o

ይኽ ትግል ዳር ሳይደርስ ወደ ኋላ አይመለስም! PART 1( መስቀሉ አየለ)ብዙ ስዎች የተጀመረውን ህዝባዊ ተጋድሎ የምጥ መጨረሻ እንዲሆናላቸው አጥብቀው ይመኛሉ። ትግሉ በአግባቡ ተይዞለውጤት እንዲበቃ በጥፍራቸው ጭምሮ ቆመው መጸልዩን ተያይዘውታል። ስጋታቸው ግን ከምን እንደ መነጨ ግልጽ ነው።የዚህን መጻጉ ቡድን ባህሪ ከመረዳት ነው። ድንገት እንደ ምርጫ ዘጠና ሰባት የከሸፈ እንደሆነ የበቀል ሰይፉን አንችለውም ከሚል ስር የሰደደ ስጋት ነው። አንድ ነገር ግን እርግጠኛ መሆን ይቻላል። ዘንዶው አከርካሪውን ተሰብሮዋል። አይድንም።ይኽ ክፉ ደዌ በምንም መልኩ እራሱን በራሱ ሊፈውስና ይኽንን ህዝባዊ አብዮት የሚቋቋምበት ምንም አይነት ቁምና ሊኖረው አይችልም ብለን ደረታችንን ነፍተን እንድንናገር የሚያስችለን ቀመር ደግሞ በጣም ግልጽና ቀጥተኛ ነው።ነጥቡም አንድ እና አንድ ነው። ሁኔታዎች መሪን ይፈጥራሉ እንጅ መሪዎች ሁኔታዎችን አይፈጥሩም ከሚል ቀመርተነስተን ነው። ይኽ በምንም መልኩ የማይለወጥ የሶሻል ዳይናሚክስ ህግ ነው።መሪዎች ሁኔታን ይፈጥራሉ ማለት ምን ማለት ይሆን?ያልታየ ያልተሰማን ነገር ካለመኖር ዎደ መኖር አምጥተው በህዝቡ ላይ ሊጭኑ እንዲሁም አዲስ ማንነት ሊፈሩጥሩይሞክራሉ ማለት ነው።ነገር ግን ያኔ የአንዲት አገር የመከራ ደዎል ጅማሮ ይሆናል ማለት ነው። መጨረሻውም እንዲህእንዳሁኑ የሁለት ዘመን ትውልድ ሙሉ ጨልጦ የጋገረ ያልተቋጨ የአብዮት አዙሪት (vicious cycle) ውስጥመውደቅ ነው። በተማሪዎች ንቅናቄም የሆነው እንዲሁ ነበር።ይህ አገር ከምን ዓይነት ድርና ማግ እንደተሰራ ምንምየማያውቁ ገራገርና ልጅ እግር ተማሪዎች ከቀደመው ትውልድ ምንም አይነት የተጋድሎ ታሪክ እርሾ ሳይወስዱ በዘመኑበነፈሰው የምስራቅ አይዲዎሎጅ (Marxism) ተነድተው ሰከሩ። ከኦሪት ጋር በተቆራኘ በግዕዝ ቋንቋ በሚያስብህዝብ ላይ ኮሚኒዝምን እናውጅ ብለው ተነሱ። አለማመን ማለት ምን ማለት እንደሆነ መዝገበ ቃላቱ በማይታወቅበትአገር ውስጥ “እግዚአብሔር የለም” አሉት። ታሪኩን ከንግስተ ሳባ እየቆጠረ በማንነቱ ሲኮራና ለማንነቱ ሲዋደቅበኖረ ህዝብ ላይ “ታሪክ የሚባል ነገር የለም፤ እንደውም ማርክስ እንዳለው የሰው ልጅ ታሪክ ሁሉ የመደብ ትግልታሪክ እንጅ አክሱም ታሪክ የዛግዌ ታሪክ ወዘተ ብሎ ነገር የለም” ብለውት አረፉት። ወድቃ በተነሳችው ባንዲራዬ፤በኀይለ ሥላሴ አምላክ ብሎ ቃሉን ለሚሰጥ ህዝብ “ንጉስ ብሎ ነገር የለም፣ ከእንግዲህስ አገሩ የወዛደር አርማውምማጭድና መዶሻ ነው” ተባብለው ተከፋፈሉ። አዲሱ ማንነታችን ብለው የወሰዱት ፤ ቦልሸቪክ ፣ ሜንሸቪክ ትሮትስካያትለሌላው ግን የሚገባ ነገር አልነበረም። “ፋኖ ተሰማራ እንደ ቸኮቬራ” የሚለው የወቅቱ መፈክር ለነፍጠኛው ባዕድቢሆን አይገርምም። ይሄ ሁሉ በግዜው ጥቂት ኮሌጅ ቀመስ ተማሪዎች ካልሆነ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ በህዝቡ ዘንድያልነበረ፣ የማይታወቅ፣ የማይገባ ባዕድ አስተሳሰብ ነበረና አንድ ትውልድ አስጨርሶ እንደ ህወሃት፣ ኦነግ መሰልተውሳክ ፈጥሮ አገሪቱም ሆነች ህዝባችን ዛሬ ለደረችበት ውርደት ትልቁን የመከራ በር ከፍቶ አለፈ። በመግቢያየላይ እንዳልኩት በሌለ ነባራዊ ሁኔታ ላይ የሚነሳ አብዮት ለምን ሳይጸነስ እንደሚጨነግፍና ይልቁንም ምን ያህልአደገኛም ጭምር እንደሆነ የተነሳበትን ሳያሳካ የትም ባክኖ የቀረው ያ ትውልድ እና አብዮቱ ትልቅ ምስክር ነው።ሁኔታዎች መሪን ይፈጥራሉ ስንል ግን ምን ማለታችን ነው?በዚህ በጣም መሰረታዊ በሆነ ጭብጥ እንዲህ አይነት ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ይኽን ሁለት ትውልድ ጨልጦ የጋገረ፣የማናመልጠው እና ያፈጠጠው እውነት አገሪቱን ሁለት መቶ አምሳ ዓመታት ወደኋላ በመመለስ ወደ ዘመነ መሳፍንትአፋፍ ላይ እየገፋ ያለ አደገኛ ክስተት መሆኑን በ አይናችን በብሌኑ እያየነው ያለ እውነታ ነው።። ራስ ስሁለሚካኤል የተባለው የትግሬ ገዥ በ፩፯ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ በእንግድነት ጎንደር ቤተመንግስት ውስጥ ባደረበትሌሊት ንጉሱን ከተኙበት አፍኖ በመግደሉ የተነሳ ኢትዮጵያ መቶ አመት ወደፈጀ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ መግባቷይታወቃል። ሁሌም ነገሮችን በተናቁ ሰዎች አድሮ መስራት የባህሪው የሆነው አምላከ ኢትዮጵያ የኮሶ ሻጯን ልጅቋረኛውን ካሳ እንደ ነቢይ በማስነሳት ታደጋት እንጅ። ከአህመድ ግራኝ ወረራና የኦሮሞዎች ወደ መሃል ኢትዮጵያመስፋፋት የተነሳ ክፉኛ የተሰባበረው የአገሪቱ ቁመና ከደረሰበት ቁስል ገና ባልጠገገበት ሁኔታእንደ ገና መቶአመት ወደፈጀ የእርስ በርስ ጦርነት በመግባቷ የተነሳ በህዝቡ ላይ የደረሰውን የመከራ ጥልቀት መስፈሪያ ቋትማግኘት አይቻልም። እንግዲ እንዲህ አይነቱ ነባራዊ ሁኔታ የፈጠረው ክፉ ቀን ነበር የዚህን ህዝብ የመከራ ግማደመስቀል የሚሸከም መንገድ መሪ ሲጣራ አጼ ቴዎድሮስን ያህል አጥቢያ ኮከብ ያገኘው።አዎ፤ ጀግና በክፉ ቀንይወለዳል ማለት ይኸው ነው።ዛሬ የተጀመረው ጸረ ወያኔ ትንቅንቅ ወደ ኋላ አይመለስም ስንል ምን ማለታችን ነው።በበታችነትና በድህነት ሰቀቀን ውስጥ የሚሰቅዩና ታሪካቸውና ዘራቸው ሁሉ ከባንዳና ከከሃዲዎች የትግራይ ገዥጉጅሌዎች የወረሱት ጀሌዎች ደደቢት በሚባል ዋሻ ውስጥ ተፈልፍለው ለአቅመ ጥፋት በደረሱ ግዜ ብዙ አለም አቀፋዊሁኔታዎች አሲረው የዚህች ታሪካዊት አገርና የዚህ መከረኛ ህዝብ እጣ ፋንታ እጃቸው ላይ ገባላቸው። አገሪቱበነርሱ ወርድና ቁመና አልተሰራችምና በልካቸው አሰፍተው ለመልበስና የበቀል ሰቀቀናቸውን ለመወጣት ያስችላቸውዘንድ አገሪቱን ከፋፍለው መግዛት ጀመሩ። በተሰባበረ መስተዋት ውስጥ እንዴት የአገሪቱን ሙሉ ካርታ ማየትእንደሚቻል ጥራዝ ነጠቁ መለስ ዜናዊ በእፉኝት ምላሱ መስበክ ጀመረ። ሞትንለት የሚሉት ህገ መንግስት የአገሪቱብሔራዊ ቋንቋ አማርኛ ነው እያለ ነገር ግን በብዙ የአገሪቱ ክፍል በዚህ ቋንቋ መጠቀም ብሄራዊ ወንጀል ተደርጎተወሰደ። አንድነት ጠፍቶ ብሄርተኝነት በይፋ ተጸነሰ። ትውልዱ ከተከለለበት አጥር አሻግሮ እንዳይመለከትተፈረደበት። ሙሶለኒ የጀመረውን አገር የማፍረስ ተልእኮ በሹምባሾቹ ልጆች ህልው መሆን ጀመረ። ይህ ድንቁርናንከጥላቻ የቀላቀለ ፖሊሲ ሲነድፉት መድረሻ ግቡ ከፋፍለህ ግዛ መሆኑ ግልጥ ነበር። ያም ሆኖ ያኔ እንዳያዩትድንቁርና ጥቁር ሰማይ ሆኖ የከለላቸው ነገር ግን ዛሬ አፍንጫቸው ስር መንቀልቀል የጀመረው እሳተ ጋሞራ አንድነትጠፍቶ ብሄርኝነት ሲያንሰራራ አደጋው በማን እንደሚከፋ ነበር። በግድ የፈጠሩት የአማራና የኦሮሞ ብሄርተኝነት ዛሬሊደበቅ የማይችል ሱናሜ ሆኖ መጥቶዋል። ዘጠና አምስት በመቶ የሆኑትን የአገሪቱን ዜጎች ወደ ለየለት ባርነትአውርዶ እንደ ባዶ ፊኛ በተወጠረ የትግራይ ተጋሩ የበላይነት እንዲሁ እየገደሉ እና እንደፈለጉ እየዘረፉ መኖርእንደማይቻል ይኽ ዓመት ምስክር ሆኖ መጣ።አይችልም። ስለሆነም ማንም የዢህችን አገር ትንሳኤ በአይነ ህሊናው ሲናፍቅ የኖረ ሰው በፍጻሜው ዋዜማ ላይመቆሙን ልብ ይበል። ባይሆን ጥያቄው በምን ያህል ዋጋ ይሄዳሉ የሚለው ብቻ ማሰቡ ሳይሻል አይቀርም። መርገምቶቹመቶ ሚሊዮን ሰው አርዶ ለመሄድ የሚያስችል በቂ ጭካኔ አለቸውና።

PART 2

ከላይ በመግቢያየ ያነሳሁትና የከሸፈው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ መሪዎችን ደርግ የተባለ የአብዮት ጠባቂዎች ስብስብ እያወጣ ሲያርዳቸው በግል ያልተነካው የህብረተሰብ ክፍል ቀርቶ የገዛ ቤተሰቦቻቸው ትንፍሽ ለማለትየቸገራቸው ልጆቻቸው ይዘው የመጡት አይዲዎሎጅ ከህብረተሰቡ ውስጥ ያልበቀለ እንግዳ ነገር መሆኑም ጭምር ነው።ስለዚህ የነበረው ግብግብ በታጠቀው የወታደሩ ክፍል እና ፊደል በቆጠሩት ተማሪዎች እንጅ ሌላውን ባለማካተቱ የትምሳይደርስ ክሬም የሆነውን የወጣት ክፍል ጨርሶ ከበላ ቦሃላ በክሽፈት ተጠናቛል።ዛሬ ግን ሌላ ቀን ነው። ትግሉ ከውጭ መጥቶ የተጫነ አይደለም ስንል ዝም ብለን አይደለም። ለሁለት አስርተዓመታት ያህል በጥላቻ፣ በዘረኝነት እና በሰይፍ እንገዛለን ብለው ከጫኑት የአገዛዝ ቀንበር የተወለደ ብሶት መሆኑነው። የኛ ከሚሏቸው ሰሜነኞች ውጭ የዚህ ግፍ ሰለባ ያልሆነ የለም። ስደት ሁለተኛ ተፈጥሯችን ሆኖ የወጣበትበተጻራራሪው ደግሞ ትግሬ መሆን ፕሮፌሽን ሆኖ የያንበት እውነት ነው። ዛሬ ሰርቶ ተምሮ ሰው መሆን አይደለምዋልድባ ገብቶ እራስን በረሃብ ለመቅጣት የነርሱ ፈቃደንነት የሚጠየቅበት አገር ባለቤቶች ሆንን። የግፉ ጥግ በዚህመልኩ ሰፍቶ ልጆቿ ገና በጽንስ ላይ እያሉ ለሽያጭ በሚቀርቡባት አገር ውስጥ ሞልቶ የፈሰሰ ግፍ ቀን ቆጥሮ መጣ።ማእበል ሆኖ መጣ። እንደ ተማሪው ዘመን ንቅናቄ የጥቂት ተማሪዎች ጉዳይ መሆኑ ቀርቶ ከህጻን እስከ ሽማግሌ፤ከከተማ እስከ ገጠር፣ ከአለማዊ እስከ ገዳማውያን ሁሉም ለግዳይ ወጥቶ ያረፈውን ይህን አስፈሪ ማእበል ወያኔየሚባል የድኩማን ስብስብ ያቆመው ዘንድ እንዴት ይቻለዋል ?..እንዴትም። እምቢ ማንነቴ ብሎ ፈንድቶ የወጣውንየወልቃይት ንቅናቄ ከአርባ ዓመት የመከራ ጉዞ ለጸሃይ ብርሃን ካበቁትና ከአብራኩ ከተወለዱት አንዱ ደመቀ ዘውዴንለወያኔ የስለት ቢላ አሳልፎ ላለመስጠት እየተከፈለ ያለው መስዋዕትነት እና በዚህ ደረጃ ለስርዓቱ ፈተናእስከመሆን የደረሰበት ዋናው ምክንያት የወልቃይት አጀንዳ ማለት ከውጭ የተጫነ ሳይሆን የወልቃይት የቁጭት ማህጸንየፈጠረውና መሪ

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: