በካንጋሮው ፍርድ ቤት የቀረቡት በነብዮ ሲራጅ የክስ መዝገብ የተካተቱት 7 ንፁሃን ሙስሊሞች ላይ አሳዛኝ ውሳኔ መተላለፉ ታወቀ

በዛሬው እለት በካንጋሮው ፍርድ ቤት የቀረቡት በነብዮ ሲራጅ የክስ መዝገብ የተካተቱት 7 ንፁሃን ሙስሊሞች ላይ አሳዛኝ ውሳኔ መተላለፉ ታወቀ

አሁን ከቀኑ 10 ሰአት ከሩብ ላይ በደረሰን መረጃ ለማወቅ እንደተቻለው የካንጋሮው ፍርድ ቤት በነብዮ ሲራጅ የክስ መዝገብ የተካተቱት 6ቱ ንፁሃን ሙስሊሞች ላይ እያንዳንዳቸው በ3 አመት ከ11ወር እስራት እንዲሁም በሁለተኛ ተከሳሽ ላይ የ3 አመት ከ3 ወር እስራት አስተላልፏል

ይህ በእንዲህ እንዳለም ይሄው የደህንነቶች ክስ ያልበገራቸውና የተሰጠው የግፍ ውሳኔ ያላንበረከካቸው ንፁሃን ተከሳሽ ጀግኖቻችን ችሎቱን በተቃውሞ ድብልቅልቁን አውጥተውታል ። የደህንነቶችን ውሳኔ ይዞ ወደ ችሎት የገባው ዳኛ በመገረምና በመደናገጥ ስነ ስርአት በሚል የተከሳሾቹን ተቃውሞ ለማስቆም ቢሞክርም ተከሳቹ በበኩላቸው ለራስህ ስነ ስርአት አድርግ እኛ ይህ ፍርድ ከየት እንደተሰጠህ እናውቃለን ድምፃችን ይሰማ ፣ መንግስት ከእምነታችን ላይ እጁን ያንሳ ፣ የታሰሩት ይፈቱ ፣ ፍትህ ለንፁሃን በሚል በከፍተኛ ድምፅ ችሎቱን ያደመቁት ሲሆን ስነ ስርአት አስከባሪ ፓሊሶችም ሁኔታውን ለማረጋጋት ያደረጉት ሙከራ አለመሳካቱን ለማወቅ ተችሏል

ቀደም ሲል የደረሰባቸው ግፍና መከራ ሳይበግራቸው ዛሬ ላይ ታሪክ የሰሩት ንፁሃን ተከሳሽ ጀግኖቻችን ዛሬ ለችሎቱ ያሳያዮት አልበገር ባይነት ለህዝበ ሙስሊሙ ታላቅ መልእክት ያስተላለፈ መሆኑንም በስፍራው የተገኙ ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል

 

Image may contain: one or more people

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: