የብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ አቡነ ማትያስ እና የጋዜጠኛ ፍሬው አበበ የፍርድ ቤት ውሎ

ተከሳሽ አቶ ፍሬው አበበ ፦፣ ቅዱስነታቸው የሚመሩት ተቋም ከከሰሰኝ አይቀር ፍርድ ቤት ቀርበው በምስክርነት ይቅረቡልኝ ። እንዲያውም በክሴ ጉዳይ ፥ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ የሚታየውን የሙስናና ብልሹ አሠራር፣ የመልካም አስተዳደር ችግር እና የመናፍቃን እንቅስቃሴ በስፋት መኖሩን ጭምር ያስረዱልኛል ። ምንም እንኳን ፓትርያርኩ ትልቅ የሃይማኖት አባት ቢኾኑም፣ በሕግ ፊት እንደ ማንኛውም ሰው በመኾናቸው ፍ/ቤት መቅረባቸው ለፍትሕ ሥርዓቱ ያላቸውን ከበሬታ ከማሳየት ባለፈ የሚነካባቸው ሞራል የለምና ቀርበው ይመስክሩልኝ በማለት ተከራክሯል ።

✔ የቅዱስ ፓትርያርኩ ጠበቃ ፦ ፓትርያርኩ፥ የቤተ ክርስቲያን መሪ በመኾናቸው እና ከፍ ያለ ማኅበራዊ ሓላፊነት ስላለባቸው፤ የሚንቀሳቀሱትም በኮር ዲፕሎማት ደረጃ በመሆኑ ፤ ቅዱስነታቸው ፓትርያርክ አባ ማትያስ ፍርድቤት በአካል ተገኝተው ቢመሰክሩ የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብርና የአማኞቿን ሞራል መንካት ስለሚኾን ቀርበው መመስከር የለባቸውም በማለት ተሟግቷል ፡፡

✔የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቂርቆስ ምድብ 2ኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ፦ ፓትርያርኩ በተከሣሽ በኩል በምስክርነት መጠራታቸው፣ መብት እንጂ ስሕተት አለመኾኑን፤ በዲፕሎማትና በሀገር መሪ ደረጃ የሚከበሩ ሰው መኾናቸው ተጠቅሶ የተደረገው ክርክርም ሕገ መንግሥቱ ጭምር እኩል ጥበቃ ያደረገለትን የእኩልነት የሕግ መርሕ የሚጥስ በመኾኑ ፍ/ቤቱ አልተቀበለውም በማለት ፓትርያርኩ እንዴት ምስክርነታቸውን ይስጡ፤ ለሚለው፣ ሕጉ፡- ምስክርነት በአካል ቀርቦ በመሐላ እንዲሰጥ ቢደነግግም፤ ፍ/ቤቱ ሲያምንበት ምስክርነቱ በጽሑፍ እንዲሰጥ ሊያዝ እንደሚችል በመጥቀስ፤ በተጨማሪም፣ ኹለቱም ወገኖች ባደረጉት ክርክር፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ባሉበት ኾነው በጹሑፍ መልስ እንዲሰጡ የግራ ቀኙ ተከራካሪ ወገኖች በመስማማታቸው፣ ፍ/ቤቱም ይህን አማራጭ ሐሳብ በመያዝ፣ ቅዱስነታቸው፣ ካሉበት ስፍራ ሆነው የምስክርነት ቃላቸውን በጹሑፍ እንዲሰጡ አዟል ። ፍርድ ቤቱ አያይዞም ፓትርያርኩ በምስክርነታቸው ስለሚያስረዷቸው ጉዳዮች በተመለከተ፣ በተከሣሽ በኩል ለታኅሣሥ 27 ጥያቄዎች ተዘጋጅተው ለችሎቱ እንዲቀርቡ፤ ጥር 2 ቀን ደግሞ፣ ከሣሽ በጥያቄዎቹ ላይ አስተያየት እንዲሰጥበት ፍ/ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

የፍርድ ሂደቱ በዚህ መልኩ ቀጥሎ መቋጫው ላይ ሲደርስ ፍትህ ለአቶ ፍሬው ከፈረደች ጋዜጠኛው ከቃሊቲም ፣ ከዝዋይም ፣ ከቂሊንጦም ሆነ ከሸዋ ሮቢት ግዞት ተርፎ በሰላም ከቤተሰቦቹ ጋር ይኖራል ። በተቃራኒው ለብፁዕ ወቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ ከተፈረደላቸው ደግሞ ጠፋ የተባለው ስማቸው በጋዜጠኛው መታሰር ምክንያት ይታደስላቸዋል ። ለዚሁም የጠየቁት የ100 ሺህ ብር ካሳም ይከፈላቸዋል ።

በነገራችን ላይ ቅዱስነታቸው በመጪው ታህሳስ 29/2009 ዓም ለሚከበረው የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ልደት ምክንያት በማድረግ ለእኛም ለመንፈስ ልጆቻቸው ፣ ለከሰሱት ጋዜጠኛ ፍሬው አበበም በቴሌቭዥን ቀርበው ” ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።. . .”ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ “። በማለት ቃለምዕዳን እና ቡራኬ በዝግጅት ላይ ናቸው ። በተቃራኒው ደግሞ ከዚሁ ጎን ለጎን ለፍርድቤት የሚቀርብ የመሟገቻ ጦማርም ያዘጋጃሉ ።

ለማንኛውም ፦

✔ ተዋህዶ ሃይማኖቴ ሆይ ፦ እግዚአብሔር ይሁንሽ ። አንገት ደፍተሽ ከመቀመጥ ተላቀሽ ቀና ብለሽ የምትሄጂበትን ዘመንም ያቅርብልሽ ።
✔ ጋዜጠኛ ፍሬው ፦ ከገንዘብ ቅጣቱም ሆነ ከአካል እስራቱ እግዚአብሔር ይጠብቅህ ።
✔ ቅዱስ አባታችን ፦ በእኔ በኩል ግድየለም ይቅርብዎ እንዳልል ስሜ ጠፍቷል ብለው ተነስተዋልና ማስቆሙ ይከብዳል ። አቤት ገራዬ መቼም ሲበዛ ወገኛ ቢጤነኝ እኮ አሁን ማን ይሙት እኔን ብሎ መካሪ ። በዚህ ላይ የካሳ ብሩም 100 ሺህ ብር ነው ። እሱም ደግሞ ያጓጓል ። የጨነቀ ነገር ገጠመን እኮ ጎበዝ ። የሆነው ሆኖ እንደኔ እንደኔ ቅዱስነትዎ የተጀመረውን ክስ ቢያቋርጡና የጠፋውን ስምዎትን እንደምንም ተረባርበን ብናድስልዎ ። ገንዘቡንም ቢሆን በእያንዳንዳችን የሚደርስብን ተነግሮን የአቅማችንን ብናዋጣልዎና ቅድስት ቤተክርስቲያንን ከውርደት ቢታደጓት መልካም ነው እላላሁ ።

ይህን የሚያጓጓም የሚያሳቅቅም ጉዳይ እስከ ፍጻሜው ድረስ በተገኘው አጋጣሚ ለመከታተል እሞክራለሁ ። ለዛሬ አበቃሁ ።

ዘመድኩን በቀለ

Image may contain: 1 person, beardImage may contain: 1 person, close-up

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: