በጀዋር መሃመድ የሚመራው (,OMN) የተሰኘ የቴሌቭዢን ጣቢያ ግብጽ ውስጥ ማንነታቸው ባለታወቁ ሰዎች እንደወደመ ተሰማ

በጀዋር መሃመድ የሚመራው (Oromia Media Network,OMN) የተሰኘ የቴሌቭዢን ጣቢያ ግብጽ ውስጥ ማንነታቸው ባለታወቁ ሰዎች እንዳልነበር ሆኖ እንደወደመ ተሰማ ካይሮ የሚገኘው ስቱዲዮ OMN የሃስት ፕሮፖጋንዳና የዘረኝነት ስርጭት በቃን በሚሉ በርካታ የኦሮሞ ብሄረሰብ ተወላጆች እና በሌሎች ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ ሲሰነዘርበት የቆየ ሲሆን በዛሬው ዕለት ነዋሪነታቸው እዚያው ካይሮ በሆኑ በርካታ ዜጎች እርምጃው እንደተከናወነ ሲገለጥ በሌላ በኩል ምናልባትም ሰሞኑን የካይሮን መንግስትን አሸባሪዎችን በመርዳት ሲከስ የነበረው እጀ ረጅሙ የወያኔ መንግስትም በእርምጃው ላይ ይኖርበታልም ተበሎ እየተገመተ ነው። የቴሌቪዥኑን ጣቢያ እንዳልነበር አድረገዉታል የተባለ ሲሆን ጠቅላላ የስቱዲዮ መሳሪያ ሙሉ በሙሉ ሊወድም ችሏል፡ ይህ ድርጊት ክፉኛ ያስደነገጠው ጀዋር ሙሃመድ በፌስ ቡኩ ገጽ ላይ በኦሮሚኛ እንደገጸው “ካይሮ የሚገኘው ጣቢያችን ላይ ጥቃቱ እንደቀጠለ ሲሆን በዛሬው እለት የስቱዲዮውን መገልገያ መሳሪያ ወደ ማውደሙ ተሸጋግረው የስቱዲዮውን መገልገያ መሳሪያ ሙሉ በሙሉ ወድሟል ሲል በመቀጠልም እንኩዋንም ሰራተኞቹ ሰላም ሆኑ እንጂ የወደሙትን መሳሪያዎች ገዝተን እንተካቸዋለን፡ደጋፊዎቻችን እንዳትደናገጡ ሁኔታውን ከሚመለከተው አካል ጋር እየተከታተልን ሲሆን የደረስንበትን ወደፊት እናስታውቃችኋለን” ሲል ደጋፊዎችን ለማጽናናት ሞክሮአል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: