ለሚመለከትው የወያኔ ድጋፍ ሰጪ አካል በሙሉ!

ለሚመለከትው የወያኔ ድጋፍ ሰጪ አካል በሙሉ! መግለጫና ምክሩ ልክ እንደናንተው ተመሳሳይ ባይሆንም አንጀት አርሱን አርበኞች ግንቦት 7ን ይመለከታል!

1. አርበኞች ግንቦት 7 የሚታገልላት ሐገራችን ኢትዮጵያን በአለቅላቂ የትግል ስልት ለመጥለፍና በወያኔ የግፍ ጅራፍ በቀጣይነት ለማስኬድ ከፍተኛ ጥረት የሚያደርጉ ግለሰቦች የጋራ ጠላታችንን በማገልገል የሚያካሄዱትን እርምጥምጥ ትንኮሳ በግንባር ቀደምትነት እቃወማለው!

2. ጀግናው የአርበኞች ግንቦት 7 ነፃነት ወይም ሞት ብሎ ዱር ቤቴ በመክተት እየከፈለ ለሚገኘው መሰዋትነት እስከ ሞት ድረስ የታመነ መሆኑን በተግባር ከማስመስከር በላይ በሰሜኑ የሐገራችን ክፍል ከህወሀት ጭንጋፍ ጋር ትንቅንቅ ውስጥ ከሚገኙ ክቡር የነፃነት ሀይሎች ጋር በመቀናጀት እያደረገ የሚገኘውን ታሪካዊ ተጋድሎ እስከ ቀራንዬ ድረስ እደግፋልው::

3. ብሄሬ በሰዋሰውነት ክብር ውስጥ የተወለደ ስጋ ሲሆን ኢትዬጵያዊነቴ ደግሞ በደምና አጥንቴ የተገነባ የመስዋትነት ውጤት ነው! ስለ ኢትዮጵያ የፈሰሰው እንዲሁም የሚፈሰው ደምና የተከሰከስው እና የሚከሰከሰው አጥንት በጎጥ አመለካከት በሰከሩ ወያኔና ወያኔያዊን እንደማይናጋ ካስመሰከረው አርበኞች ግንቦት 7 ጋር በክብር እቆማለው::

4. ህዝቦች በመደራጀት ተደራጅቶም ወደ ፊት መራመድ እንዲችሉ ባለኝ አቅም ሁሉ አግዛለው ነገር ግን አንዳንድ ግለሰቦች በመደራጀት ፍላጎት ብቻ ተነሳስተው በሰፊው ህዝብ የትግል ምእራፍ ላይ መቀለዳቸውን እንዲያቆሙና ወይኔን ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ለመደምሰስ በሚደረገው የጋራ እርብርብ የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስባለው!

5. የአርበኞች ግንቦት 7 አባላቱ አላማ የሚሰውላት ኢትዮጵያ ሐገራችን ነጻነት ሲሆን! እርሱም የመሰዋትነት ተግባራቱ በውጤት ተፈትኖ የድል በራፍ ላይ መድረሱን ለማሰናከል ከሚጥሩ አካላቶች ፍላጎት በላይ መሆኑን በክብር እያስመሰከሩ የሚዋደቁለት ህዝብም ከጠላቶቻችን ሴራ በላይ መገስገሱን በማረጋገጥ በአጥንታቸው ማገርነት የእናት ኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ከፍ አድርገው ለማውለብለብ እና የማይቀረውን የሁላችንም የጋራ ፍልጎት የነፃነትን ችቦ በህብረት ለማንቦግቦግ በቃል ኪዳን የተሳሰሩ በመሆናቸው ለተራ መግለጫና ትንኮሳ ግዜ እንደሌላቸው በመምከር በከንቱ የሚደክሙትን ግለሰቦች ሰከን እንዲሉ አሳስባለው::

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ! ድል ለጀግናው አርበኞች ግንቦት7!

ጉድሽ ወያኔ

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: