በጎጃም ፍኖተ ሰላም የተካሄደውን የመምህራንና ተማሪዎች አድማ ተከትሎ በርካቶች ታሰሩ

የፍኖተ ሠላም መምህራን ኮሌጅ፤ የሃይሉ ኮሌጅና የምዕራብ ጎጃም አጠቃላይ የሙያና የቴኪኒክ ትምህርት ቤት ተማሪዎችና መምህራን በጀመሩት በዚህ ተቃውሞ በከተማው የሠፈረው የአጋዚ ጦር በነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ወከባና እንግሊት እየፈጸሙ እንደሚገኝ ታውቆአል። አድማው እየተካሄደባቸው ባሉት ትምህርት ተቋሞች አጎራባች የሚገኙ ሱቆችና ንግድ ድርጅቶችም አገልግሎት መስጠት በማቋረጣቸው የአድማው ተባባሪ ተደርገው ለዕስርና እንግልት እየተዳረጉ ናቸው።

በሶስቱም ትምህር ቤቶች የተጀመረውን አድማ አስተባብረዋል የተባሉ መምህራንና ተማሪዎች ከየሚኖሩባቸው ቤቶች እየታደኑ ለእስርና ለድብደባ  መዳረጋቸውን ያስታወቁ ምንጮች አንዳንድ ለሆዳቸው ያደሩ የቀበሌ ተመራጮችና አስተዳዳሪዎች ለመከራ የተዳረገውን ወገኖቻችውን እያፈነና እያሳደደ ላለው የህወሃት አጋዚ ጦር አሳልፈው ለመስጠት የሚኖሩባቸውን ቤቶች እየጠቆሙ እንዳስያዙዋቸው ተገልጾአል። በፍኖተ ሠላም ያለፈው ረቡዕ የተጀመረው ትምህርት የማቆም አድማ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ዛሬ አርብ ከሰዓት ቦኋላ ድረስ ቀጥሎአል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ህወሃት ለፍኖተ ሠላም ወጣቶች በነገው ቅዳሜና ዕሁድ ታህሳስ 22ና 23 አዘጋጅቶት የነበረው የተሃድሶ ሥልጠና  ተቃውሞ እንደገጠመው ታውቆአል። ተለውጠናል የሚል በትልቁ ተጽፎ መሃል ከተማው ላይ እንዲቆም የተደረገው ቢል ቦርድ ማንነታቸው ባልታወቁ የከተማው ወጣቶች ተነቅሎ የት እንደደረሰም አለመታወቁ ከተማውን ለማረጋጋት ደፋ ቀና በሚሉት የህወሃት ሰዎች ላይ ግራ መጋባትን ፈጥሮአል። በተሰቀለ በሁለተኛው ቀን ተነቅሎ የተሰወረው ተለውጠናል የሚለውን ቢል ቦርድ ፍለጋ የቤት ለቤት ፍተሻም ተካሂዶ ውጤት አልተገኘም ተብሎአል።

በተያያዘ ዜና ከደብረልባኖስ ገዳም ተሰውረው ፍኖተ ሰላም ወደሚገኘው ቁስቋም ገዳም ተደብቀዋል የሚባሉ ሁለት የእምነት  አባቶችን ፍለጋ ህወሃት እየተሯሯጠ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ሁለቱ አባቶች ህወሃት በአገራችንና በህዝባችን ላይ እየፈጸማቸው ያሉትን ወንጀሎች የሚያወግዙ በመሆናቸው በሽብርተኝነት የተፈረጁ ናቸው ያሉት ምንጮች ሁለቱን ፍለጋ ቁስቋም የሚገኙ መንኩሳትንና የገዳሙን ነዋሪዎች አፈናቅለው ወደ ባህታ ቤተክርስቲያን እንደወሰዱዋቸው አረጋግጠዋል። የፍኖተ ሠላም ህዝብ አገዛዙ በከፈተባቸው የአፈና ዘመቻ ላለመንበርከክ ካለፈው ሃምሌ ወር ጀምሮ ከፍተኛ ትንቅንቅ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: