በሀገሪቱ ዉስጥ የሚገኙት ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካንፖች የስልጠና ሂደት በማቆም ላይ መሆናቸዉን ምንጮቻችን ገለፁ

99994-430426_159963350831423_915461233_n

በዋናነት የሚታወቁት ጦላይ፣ ሁርሶ፣አዋሽ ሰባት ኪሎ ብላቴ እና ብርሸለቆ የተባሉ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካንፖች ካለፉት ሁለት አመት ተኩል ወዲህ የሚያሰለጥኗቸዉ የአዲስ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ሰልጣኞች ቁጥር እየተመናመነ በመምጣት በተከታታይነት ይሰጥ የነበረው ስልጠና ሙሉ በሙሉ አቁሟል ሊያስብል ከሚችልበት ደረጃ መድረሱን  የደረሰ መረጃ አመለከተ ።

መረጃውን ለዝግጅት ክፍላችን ያደረሱ የውስጥ ምንጮች እንደሚሉት በጦላይ እና በብርሸለቆ ባለፈዉ አመት የብሄር እና የፖለቲካ አቋምን መሠረት ባደረገ መስፈርት ተመልምለው በማዕከሎቹ ስልጠና ከተሰጣቸዉ 4 ሺ ሰልጣኞች መሀል የስልጠናዉን ጊዜ አጠናቀዉ ለምረቃ የበቁት ከ8 መቶ ያነሱ ብቻ ነበሩ። ወደ ሥልጠና ከገቡ ቦኋላ ከመመረቃቸው በፊት አቋርጠው ከተመለሱት በርካቶች መካከል ግማሽ የሚሆኑት በተለይ ከሚደረግባቸዉ የብሄር ተኮር ጫና የተነሳ የተለያዩ ሰበቦችን በመስጠት ስልጠናዉን አቋርጠዉ መዉጣታቸዉን እና መጥፋታቸዉን እንዲሁም ጀርባችሁ መጠናት አለበት እየተባሉ ተወስደዉ ያለተመለሱም እንደሚገኙበት ታዉቋል።

እንደ ምንጮቻችን ገለፃ ወታደራዊ ካንፖቹ በአሁኑ ሰዓት በፈቃደኝነት ገብተው የሚሰለጠኑ ሰልጣኞችን ለማግኘት ባለመቻሉና እና በግዳጅ ተይዘው በሚላኩለት አዳዲስ ሰልጣኞች ላይ ደግሞ ባለሥልጣናቱ እምነት በማጣታቸዉ ከፍተኛ ግራ መጋባት እንደተፈጠረ ተገልጾአል።በዚህም ምክንያት ባዶ እየሆኑ የመጡት የማሰልጠኛ ካንፖች ህዝባዊ አመፁ ከተቀሰቀሰ ወዲህ ከየክልሉ እየታፈሱ በሚመጡ እስረኞች ተሞልተዋል ተብሎአል። በአብዛኛው አገሪቱ ክፍል በተፈጠረው ህዝባዊ እምቢተኝነት ምክንያት ታፍሰው በነዚህ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች እስር ላይ ከሚገኙ በርካታ ታሳሪዎች መካከል በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞች ካለፈዉ ሳምንት ጀምሮ ለጥልቅ ተሀድሶ ትፈለጋላችሁ ተብለው ወደ አልታወቁ ቦታዎች እየተወሰዱ እንደሚገኙም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

የህዋት አገዛዝ አስቀድሞ ያሰለጠናቸዉን እና በተለያየ ምክንያት ስራቸዉን እንዲለቁ ያደረጋቸዉን የመከላከያ እና ፖሊስ አባላት አሁን እየገጠመዉ ላለዉ የሰልጣኞች እጥረት ማሟያ እንዲሆን በተደጋጋሚ ጥሪ እያደረገ ቢገኝም ከቀድሞ አባለቱ ተቃዉሞ እና ወቀሳን ያዘሉ አስተየቶችን እንጂ አዎንታዊ ምላሽ ሳያገኝ መቅረቱ በተደጋጋሚ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ሲዘገብ መቆየቱ ይታወሳል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: