ሰመራ ዩንቨርስቲ አዲስ የተሰራው እስቶር በእሳት ነደደ

ሰመራ ዩንቨርስቲ አዲስ የተሰራው እስቶር በእሳት ነደደ። ከሬጂስትራል ጀርባ የሚገኘው አዲሱ እስቶር ምንም እንኳን ከተማሪወች ዶርምታሪ የራቀ ቢሆንም መነሻ ምክንያቱ ባልታወቀው የእሳት አደጋ በክፍሉ የነበሩ እያንዳንዱ እቃ በእሳት ሙሉ በሙሉ ጋይተዋል። ኮምፒተሮችን፣ የመኪና ጎማወችን፣ሰሌዳውችን፣ የፅህፈት መሳሪያወችንና መሰል የዩንቨርስቲው ንብረቶችን የያዘ ነበር። ዕለተ ሐሙስ ከምሽቱ 2 ስዓት እስከ 5 ሰዓት የዘለቀው የእሳት አደጋ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ የነበረ ቢሆንም የእሳት አደጋ ሰራተኞችን ጨምሮ መከላከያ ሰራዊት በስፍራው እንደደረሱ ለማወቅ ተችሏል።

በተማሪወች ላይ ምንም አይነት ጉዳት የደረሰ ባይኖርም ከግቢ እንዳይወጡ ተከልክለው እንደነበር ታማሪወች ይናገራሉ። እጅጉን በሚያስፈራው የእሳት አደጋ በሰዓቱ በጊቢው መብራት መጥፋቱ ጋር ተደማምሮ ጭንቀታቸውን ጨምሮት እንደነበር ተናግረዋል።

ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት በእሳት አደጋው ወድሟል። በሰመራ ዩንቨርስቲ ግቢ አሁንም ውጥረቱ እንዳለ ይገኛል። በአፋር ሎጊያ፣ አሳይታ፣ አፍዴራ.. ከቀናት በፊት ህዝባዊ አመፆች እየተነሱ እንደሆነ ታውቋል።

aseac

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: