ኮ/ል ደመቀ ከአርበኞች ግንቦት 7 ትእዛዝ በመቀበል አገርን በማወክ ክስ ተመሰረተባቸው

ኮ/ል ደመቀ ከአርበኞች ግንቦት 7 ትእዛዝ በመቀበል አገርን በማወክ ክስ ተመሰረተባቸው

በአዲስ አበባ የሚገኘው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማክሰኞ በ18 ቀን 2009ዓም በዋለው ችሎት በኮሎኔል ደመቀና በአስራ ሶስት (13) የወልቃይት ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ላይ አቃቤ ህጉ ያቀረበውን የክስ መዝገብ ተመልክቷል።

ከአርበኞች ግንቦት 7 ቀጥታ ትእዛዝ በመቀበል ሃገሪቷን አውከዋል በማለት ወያኔ በአቃቢ ህጉ በኩል ኮሎኔል ደመቀንና አስራ ሶስቱን (13) የወልቃይት ህዝብ የአማራ ማንነት ጠያቂ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላትን ከሷል።

ተከሳሾቹ በትግራይና በጎንደር የሚገኙትን የክልል ባለስልጣናትን በማፈንና በመግደልም ውንጀላ በአቃቢ ህጉ ተጨማሪ የክስ መዝገብም ተከፍቶባቸዋል።

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የወያኔን አስራ አንድ (11) የመንግስት ታጣቂዎችን ገድሏል ሰባቱን (7ቱን) ደግሞ አቁስሏል በማለት አቃቢ ህጉ ክሱን ለችሎቱ አሰምቷል።

በጎጃምና በጎንደር በግምት ከሃያ ሚሊዮን (20ሚሊዮን) ዶላር በላይ ለሆነ ንብረት ውድመት ተከሳሾቹ ተጠያቂ መሆን አለባቸው የሚል ውንጀላም አቃቢ ህጉ አቅርቧል።

አምስቱ ተከሳሾች ማክሰኞ በአዲስ አበባ በዋለው ችሎት እንደቀረቡ መረዳት ተችሏል።

ኮሎኔል ደመቀ በጎንደር አንገረብ እስር ቤት ሲሆኑ ወደ አዲስ አበባ ለማዘዋወር የወያኔ መንግስት ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራዎች በአማራ ቆራጥ ህዝብ ተጋድሎ መክሸፉ ይታወቃል።

ከተካሳሾቹ መካከል ስድስቱ (6) በአዲስ አበባ ማእከላዊ እስር ቤት ሲገኙ የተቀሩት ዘጠኙ (9) በጎንደር ታስረው ይገኛሉ።

ችሎቱ ለተጨማሪ ምርመራ የክስ መዝገቡን ለጥር 4 ቀን 2009ዓም ቀጥሯል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: