የሳምንቱ አበይት ዜናዎችና ሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮችን የምንዳስስበት የሬዲዮ ዝግጅት ያዳምጡ

ኮሎኔል ደመቀን አናስወስድም ባሉ እስረኞች ላይ ወያኔ ኢሰባዊ ድርጊት የፈፅመ ነው ተባለ

ጎንደር ከተማ  አንገረብ እስር ቤት አሁንም ውጥረቱ እንደተባባሰ ቀጥሏል የተባለ ሲሆን። ኮሎኔል ደመቀን አናስወስድም ባሉ እስረኞች ላይ እስከ እረፋዱ ድረስ የዘለቀ ተኩስ ተከፍቶባቸዋል። ስለደረሰ ጉዳት እስካሁን የታወቀ ነገርባይኖርም የተገደሉ እስረኞች ስለመኖራቸው ይነገራል ።

ሜን ሸዋ መራህቤቴ አካባቢ መሳሪያቸውን ሊገፍ የሄደን የወያኔ ቅጥረኛ ድባቅ መትተው የሸኙት  ጀግኖቹ መሬዎች ሁለት ቅጥረኛ ገለው መሣሪያቸውንም ቀምተው ተሰውረዋል ተብላል። በዚህ የተደናገጠው ወያኔ ከደብረብርሃን ጭምር ሃይል አስመጥቶ  በጉዳዩ የሌሉ ብዙ ሰወችን ደብድብው ወደ 15 ማሰራቸው ተነግራል። ጀማና ውንጪት አካባቢ መንገድ እንደተዘጋጋ መረጃ ከቦታው ደርሶናል። በተጨማሪም
በደባርቅ ከተማ  ጭንቅ ውስጥ የገባው ወያኔ በሌላ ዙር ወጣት እስካዛውንት ድረስ እያሰረ መሆኑም የተነገረ ነው።

የአምቦ ተማሪዎችን ተቃውሞ ተከትሎ በኦሮሚያ አዲስ ውጥረት መንገሱ ተነገረ

በአምቦ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ዶ\ር መረራ ጉዲና አቶ በቀለ ገርባና የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ የተቃውሞ ትእይንት አደረጉ።

ህወሃት እስረኞችን “አሰልጥኜ” አስመረኩ አለ፤ እስረኞቹ “ በፍፁም፣ አይደገምም፣ የቀለም አብዮት፣ ህገ መንግስት እና የኢትዮጵያ ህዳሴ” የሚሉ ኮርሶች የወሰዱ ናቸው።

ህወሃት አምስት ሺህ የሚጠጉ እስረኞችን “ተመራቂዎች” በሚል መፍታቱን ይፋ ባደረገበት ቀን በተመሳሳይ አምቦ ተማሪዎች ተቃውሞ ማሰማታቸው ተሰማ።

በአምቦ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ዶ\ር መረራ ጉዲና አቶ በቀለ ገርባና የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ የተቃውሞ ትእይንት አደረጉ። በጊንጪ፣ በጉደር ፣በኣወዳይና ሻሸመኔ ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ ጥበቃና አሰሳ እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል። የኣስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳና ሕወሓት ስልጣን እንዲለቅ ተቃውሞ ሲያሰሙ ውለዋል።ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሶስት የመንግስት መኪኖች ጥቃት እንደደረሰባቸው ታውቋል።

 

በሰሜን ጎንደር በህዝቡና በወያኔ መካከል ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው 

የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባላት የሆኑት አቶ ዘውዱ ገ/እግዚያብሄርና አቶ ሙላው ከበደ በመተማ ወረዳ ልዩ ስሙ ስናር በተባለው አካባቢ በወያኔ መከላከያ ሰራዊት ተከበው የነበረ ሲሆን ከዚህ ከበባ ለመውጣት ከስርዓቱ ታጣቂ ሃይሎች ጋር ውጊያ በማድረግ አቶ ዘውዱ ገ/እግዚያብሄር 5 የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ገድሎ እርሱም በክብር ተሰውቷል፡፡ ወያኔም እነዚህን ሁለት ሰዎች አስከሬን አይቀበርም ብሎ በጠራራ ፀሃይ መሬት ላይ አስጥቶ እንዲውሉ ቢያደርግም የአካባቢው ህዝብ ባደረገው ጫና ምክንያት ህዝቡ ቃፍታ ወስዶ ቀብሯቸዋል ፡፡

ከዚህም ጋር ተያይዞ በአካባቢው ብዛት ያላቸው ታጣቂዎች ማይሰገን ከተባለ ቦታ ከህዝብ ጎን በመቆም አንዳነድ እንቅስቃሴዎችን እያደረጉ መሆኑ የታወቀ ሲሆን አንድ የወያኔ ሰላይ የሆነና በኢንቨስተር ስም በአካባቢው የሚኖር በርሄ ጎሼ የተባለ የአገዛዙ ሰላይ ልጁና ወኪሉ በታጠቁ ሃይሎች ተጠልፈው የተወሰዱ መሆኑን አስታውቀው መረጃው ህዝብን እምባ እናብሳለን በሚል ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆናቸውንም ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ይህንን የህዝቡንና የታጣቂዎችን እንቅስቃሴ ተከትሎ ወያኔ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የገባ ከመሆኑም ባሻገር አብደራፊ ዳንሻና ሁመራ አካባቢ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት እያሰፈረ እንዲሁም በአካባቢው ያጠራጠራቸውን ሰዎች ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል ብዛት ያላቸው ሰዎችን በየጦር ካምፑ አገዛዙ በግፍ እያሰረ እየደበደበ መሆኑ ታውቋል፡፡

//በጋምቤላ ክልል ሰፋፊ የእርሻ መሬት የወሰዱ 29 ድርጅቶች የገቡበት አልታወቀም ተባለ

በጋምቤላ ክልል በኢንቨስትመንት ስም ተመዝግበው ሰፋፊ የእርሻ መሬትን የወሰዱ 29 ድርጅቶች የገቡበት አለመታወቁን ከክልሉ መሬት አሰጣጥ ጋር ተፈጥሯል የተባለን ችግር እንዲያጠና የተቋቋመ ቡድን ይፋ አደረገ።
ከአንድ አመት በላይ ጥናቱን ሲያካሄድ የቆየው ይኸው ቡድን በጋምቤላ ክልል ለኢንቨስትመንት ከተሰማሩ 623 ባለሃብቶች መካከል ለ381 ባለሃብቶች የተሰጠው ከ45ሺ ሄክታር በላይ መሬት ተደራርቦ እንደተሰጣቸው ተመልክቷል።
የተደራረበ መሬት የተረከቡት እነዚሁ 381 ባለሃብቶች ከኢትዮጵያ ልማት ባንክና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በብድር መውሰዳቸውንና ድርጊቱ በመንግስት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ማድረሱም ታውቋል።
ከባለሃብቶች መካከል 29 የሚሆኑት የገቡበት አልታወቀም።ሆኖም ግን ድርጅቶቹ ምን ያህል መሬት ተረክበው እንደነበርና የወሰዱት ብድር መጠን ሳይገለጽ ቀርቷል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ልዩ ትዕዛዝ ጥናትን እንደሚያካሄድ ተቋቁሞ የነበረው የባለሙያዎች ቡድን በጋምቤላ ክልል ለሰፋፊ እርሻዎች ከተሰጠ 630 ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥ ወደ ልማት የገባው ከ15 በመቶ እንደማይበልጥ ማረጋገጡን ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን አስታውቋል።
የህንድ ኩባንያዎችን ጨምሮ በርካታ ኩባንያዎች በክልሉ መሬትን ተረክበው ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከፍተኛ ብድርን ከወሰዱ በኋላ የገቡበት አልታወቀም ተብላል

 

 

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: