ወያኔ በጎንደር የወረዳና የቀበሌ አመራሮችን ማሰር ጀመረ

በጎንደር ያለው አለመረጋጋት አሁንም እንዳየለ ሲሆን በ አማራ ታጋዮች እና በትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮችና ተላላኪዎቹ መካከል የሚደረገው የሞት ሽረት ውጊያም እንደቀጠለ ነው።

በጎንደር ህዝብ ላይ እምነት ያጣው የትግራዩ መንግስት በዚህ ሳምንት ታቦት ይዘን አንወጣም ሃይማኖታችንን ለፖለቲካ መጠቀሚያ አናረክስም ያሉ የሃይማኖት አባቶችን አፍሶ ማሰሩን ዘሐበሻ የዘገበች ሲሆን ዛሬ የተሰማው መረጃ እንደሚጠቁመው ደግሞ ሕወሓት በጎንደር ያሉ የወረዳና ቀበሌ ባለስልጣኖቹዋን ለድርጅቱ ታማኝ አይደሉም የገበሬውን ተጋድሎ ይደግፋሉ በሚል ማሰሩዋን ከ አክቲቭስት ሙሉነህ ዮሀንስ የተገኘው መረጃ አመልክቱዋል።

እንደ አክቲቭስቱ ገለጻ ከነዚህ የስር ዓቱ ተላላኪዎች እስር በተጨማሪ በዛሬው እለት በጎንደር ወጣቶችን ለማፈስና ወደ ብርሸለቆ ለመውሰድ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው። በጎንደር ያሉ ወጣቶችም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪም ቀርቡዋል። በተለይም ይህመረጃ የደረሳችሁ ወገኖች መረጃውን በሶሻል ሚዲያዎች በማጋራት ወጣቶቹ የ አፈሳውን መረጃ እንዲሰሙና እንዲጠነቀቁ እንድታረጉ ጥሪ ቀርቧል።

15354184_682255945273072_1620739714_o

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: