በልደታ ክ/ከተማ የመሰረት ጉድጓድ በመቆፈር ባሉ 14 ሰራተኞች ላይ የህይወትና የአካል ጉዳት ደረሰ።

በዘርይሁን ሹመቴ

በኢትዮጵያ በግንባታ መስክ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሰራተኞች ላይ እየደረሰ የሚገኘው ጉዳት እየጨመረ መሆኑን ታወቀ። በገዢው ፓርቲ አጽንኦት የሚሰጠው መሬትን ለባለሃብት በልማት ስም የመቸብቸብ ሂደት እንጂ በልማቱ ወይም በግንባታዎች ላይ ተቀጥረው ቤተሰባቸውን ስለሚያስተዳድሩት ሰራተኞች ደህንነት አለመሆኑ በየአመቱ ቁጥሩ እየጨመረ የሚገኘው የአካልና የነፍስ መጥፋት ጉልህ ማሳያ ነው። በቅርቡ ከአማራ ክልል በግንባታ መስክ ላይ በቀን ረዳትነት ተቀጥረው ለመስራት ወደ አዲስ አበባ ያቀኑት 4 ወጣቶች ህይወታቸው በሚያሳዝን መንገድ ለህልፈት ተዳርጓል። እነዚህ ወጣቶች ስራውን ከጀመሩ ገና 9ኛ ቀናቸውም እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል። አደጋው የተከሰተው ማክሰኞ ኅዳር 4 ቀን 2009 .. ከቀኑ 7 ሰዓት ገደማ ሲሆን ፤ የሟቾቹን አስክሬን ለማውጣት ከ 5 ሰዓታት በላይ እንደፈጀም ለማረጋገጥ ተችሏል።

32 የቀን ረዳቶች ቀጥሮ በልደታ ክፍለ ከተማ በተለምዶ አብነት አከባቢ እየተገነባ ያለው የባለ 20 ፎቅ ህንጻ ለ4ቱወጣቶች ነፍስ ማለፍና ለ4 ተጨማሪ ሰራተኞች የአካል ጉዳት መድረስ መንስኤ ሆናል። ለዚሁ አደጋ ምክንያት ከ10 ሜትር በላይ ጥልቀት በሚደርስ መሬት ውስጥ ለህንጻው የመሰረት ጉድጋድ በመቆፈር ላይ ባሉ 14 ሰራተኞች ላይ የደረሰ ናዳ እንደሆነ እማኞች ተናግረዋል። በባለፉት 5 ወራት ብቻ ከህንጻ ግንባታና ከቁጥጥር ማነስ ምክንያት የተነሳ ከ24 በላይ የቀን ረዳቶች ለሞት መዳረጋቸው ተረጋግጣል። ከዚህም በተጨማሪ ከ34 በላይ በህንጻ ግንባታ ውስጥ በቀን ረዳትነት በሚያገለግሉ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት እንደደረሰ መረጃዎች ይፋ ያደርጋሉ።

በተደጋጋሚ የሚከሰተው እንደዚህ ያለ ዘግናኝ አደጋ የመንግስት ቸልተኛነትና የስርአቱ በሙስና መጨማለቅ ውጤት ነው ለሚባለው ጥያቄ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ኤጀንሲ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት አቶ ንጋቱ ማሞ ከመንግስት ይልቅ በላባቸው እራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ለመርዳት በሚተጉት የቀን ረዳቶች ላይ ጣታቸውን በመቀተር ወቀሳቸውን ሰንዝረዋል። የህዝብ ግንኝነት ባለሙያው በማከለም የቀን ሰራተኞች ጉልበት እንጂ እውቀቱ የላቸውም በማለት ለሚደርሰው አደጋ የባለሃብቶቹ አልያም የመንግስት ሃላፊነት እንዳልሆነ በሚያሳይ አኳሃን ገልጸዋል። በከተማው በመንግስትና በግል የህንጻ ግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ በቀን ረዳትነት ተቀጥረው ለሚሰሩ ሰዎች መደረግ የሚገባ የአደጋ መከላከያ ቅድመ ጥንቃቄዎችና ህጎች በሚመለከተው የመንግስት አካል ችላ በመባሉ ምክንያት እየጨመረ ላለው ለሰው ህይወት መጥፋትና አካል ጉዳት ዋንኛ ምክንያት ሆነዋል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: