በደባርቅ ወረዳ የቦዛ ድምብልግሳ ቀበሌ ተወላጅ የሆነዉ የልዩ ሀይል ኢንስፔክተር በዛብህ ተገደለ።
December 15, 2016 Leave a comment
በደባርቅ ወረዳ የቦዛ ድምብልግሳ ቀበሌ ተወላጅ የሆነዉ የልዩ ሀይል ኢንስፔክተር በዛብህ ተገደለ። ከወያኔ ጋር በሚሊሽያነት የሚያገለግሉ የአካባቢው የአማራ ተወላጆች ስርአቱን እየጣሉ እየወጡ ነው። ለተቀሩትም ህዝቡ ጥሪና ማስጠንቀቂያ እያስተላለፈላቸው ነው። ወያኔ የአማራውን ህዝብ እርስ በርስ እንዲገዳደል የዶለተውን ሴራ ተገንዝበው ለወያኔ ያደሩ ሆዳሞች ከህዝባቸው ጎን እንዲቆሙ ግፊቱ አይሎባቸዋል። ለወያኔ አልታዘዝ የሚሉት ብዛታቸው እየጨመረ በመሆኑ ወያኔ ተደናግጣ ታማኝ ያለቻቸውን ሁሉ እያሰረ ይገኛል።
በቆላማው ወገራ በሰነበተው ውጊያ የወደቀውን አስከሬን አንሱ አምጡ በማለት ወያኔወች ወጣቶችን እያስገደዱ ነዉ። ምክንያቱም ደፍሮ ቆላ የሚወርድ በመጥፋቱ ነው።
በተያያዘ ዜና ከዳባት ከተማ ወደ ቆላዉ ለወያኔ ሰራዊት ራሽን እንዲያጓጉዙ የ4 ቀበሌዎች ሊቀመናብርት በማስጠራት በየቀበሌው 10/10 ወጣት እንዲያቀርቡ ትእዛዝ የተሰጠ ቢሆንም የሚተባበር ማግኘት ተስኗቸዋል። በወያኔ ውስጥ ፍርሃት ነግሷል።
፨እንድታውቁት! ወያኔ 21 ሰላማዊ ሰወችን “ሽፍታ” ማርከናል በማለት ለሚዲያ ሊያቀርቡ እየተዘጋጁ እንደሆነ መረጃ ደርሶናል። ስለዚህ ከእዉነት የራቀ መሆኑ ከወዲሁ ይታወቅ።
በተጨማሪም ህፃናት፣ ሴቶችንና አቅመ ደካማ ሽማግሌወችን ውጊያ ከሚደረግባቸው አካባቢወች በማሰር ወደ ጎንደር ከተማ እያመጡ መሆኑ መረጃ ስለደረሰን የከተማው ህዝብ ደህንነታቸውን እንዲከታተልና ከእስር እንዲያስለቅቃቸው ጥሪ ቀርቧል።