በዳባት ወረዳ በጃኖራ ቀበሌ ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው ጦርነት ዛሬ ቀጥሎ ውላል

በዳባት ወረዳ በጃኖራ ቀበሌ ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው ጦርነት ዛሬ ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ ታጋዮች የያዙትን ምሽግ ሰብሮ መግባት ያልቻለው የአገዛዙ ጦር፣ ከባድ መሳሪያዎችን በመተኮስ የስነ ልቦና ጫና ለመፍጠር እየሞከረ ነው። ከጦር ግንባሩ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በአካባቢው በብዛት የሰፈሩት ወታደሮች ሞርታርና ዲሽቃ እየተኮሱ አካባቢውን ሲደበድቡ ውለዋል። የግንባሩን ቃል አቀባይ በቀጥታ ለማግኘት ባንችልም፣ ከአካባቢው ምንጮች እንዳገኘነው መረጃ ከሆነ ዛሬ 5 የገዢው ፓርቲ ወታደሮች ተገድለዋል። በአቶ መሳፍንት ተስፉ የሚመራው ተዋጊ ሃይል ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከ60 በላይ ወታደሮችን መግደሉን እና በርካታ የጦር መሳሪያዎችን መማረኩን መግለጹ ይታወቃል። የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት የደረሰበትን ሽንፈት ተከትሎ የመሪውን የአቶ መሳፍንትን ሁለት ቤቶች ጨምሮ በጦርነቱ ይሳተፋሉ ያላቸውን አርሶአደሮች ቤት አቃጥሎአል። የእህል ክምራቸውንም እንዲሁ በእሳት አቃጥሎአል። በሌላ በኩል ደግሞ ሻለቃ ፈንቴ ወይም በተለምዶ ሙሽሬ እየተባለ የሚጠራው ነባር ታጋይ በሰሞኑ ውጊያ ተገድሎ ጎንደር ላይ የቀብር ስነ ስርአቱ መፈጸሙን ምንጮች ገልጸዋል።

04356-barefoot2btplf2bsoldiers2b-2bethiopia

 

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: