ሀገራችንን ወደ ማያባራ እልቂት የሚመራት ጎሰኝነትና የጎሳ ፖለቲካ ነው

ጎሠኝነት በክልል፧በአውራጃ፧ በወረዳ፧በቀበሌ፧በመንደጨር ጠቦ ጠቦ ወደቤተሰብ ይሄዳል!! ትዳር ያለያያል፧ ልጆች ያለአሳዳጊ ይቀራሉ ። የዜጎች በሠላም በፍቅር አይኖሩም። የጎሳ መሪዎች በመፎካከር በሚቀሠቅሱት ጦርነት ንፁሀን ዜጎች ወደማያባራ የጦርነት እልቂት ይገባሉ። በዚህ ወቅት የአገር እድገት ብልፅግና አይታሠብም። በሚቀሠቀሠው ጦርነት የውጭ ሀይሎች መሣርያዎቻቸውን ይቸበችባሉ። የአገሪቱን ጥሬ ሀብት ይዘርፋሉ። በሩዋንዳ፧በሶማልያ …..ወዘተ እንደታየው መሆኑ ነው። የጎሳ ፓለቲከኞችና ደንታ የሌላቸው መሪዎቻቸው በገንዘብ ኪሳቸውን ይሞላሉ።
ወገኖቼ ኢትዮጵያውያን ብታምኑም ባታምኑም ቅድስት አገር ኢትዮጵያችን ላይ ያንዣበበው ጥቁር ዳመና ይሄ ነው። አዎ ዛሬ በኛ ትውልድ። አያሳዝንም?! ነገ ኢትዮጵያ የምንላት ውድ አገራችንን ማጣትና በብዙ ሚጢጢ የጎሳ መሪዎች የተከፋፈለች ሀገር ማየት የሚፈልግ አለ?!!!
አዎ ዛሬ ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች!!!?
በጎሠኛ አውሬ መሪዎች ተከባ እንደቅርጫ ሥጋ ሊቀራመቷት ቢላዋቸውን እየሳሉላት ነው!
ወገኖቼ እነዚህን ነጋዴዎች በቃችሁ ማለት የሚገባን ዛሬ ነው። አንዴ ካመለጠች ኢትዮጵያ አትገኝም። እኛንም የዚህ ዘመን ትውልዶችን ለዛች ሀገር አጥንታቸውን ከስክሠው ደማቸውን አፍስሰው ያቆዩን ያአባት ያያቶቻችን አፅም ይወቅሠናል!! “ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ” ከታሪክ ተወቃሽነት እንዳን። ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት በሚደረገው የነፃነት ትግል ውስጥ እንደየአቅማችን ተሳትፈን የትግሬ ነፃ አውጭ ነኝ ብሎ ራሱን የሚጠራው ጎሠኛና የነፍሰገዳዮች የቡድን አገዛዝ አገራችን ነፃ እናውጣ።

13819494_611651515666849_1114674654_n

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: