ከቆላማው ወገራ የጦር ግንባር ልዩ ሪፖርት! – ምክትል ሳጅን ዋጋየ ጫቅሉ በጦርነቱ መገደሉ ተነገረ

እኛ በቆላማው ወገራ ጥረን ግረን የምንኖር ገበሬወች ላይ በግፈኛው ወያኔ በህልውናችን ላይ የተቃጣብንን ጥቃት እውነትንና ፈጣሪን ይዘን ተከላክለን እያጠቃን እንገኛለን። ሁለተኛ ሳምንቱን ያስቆጠረው ጦርነት አሁንም ለአምስተኛ ዙር 11 መኪና ሞልተው በላኩት መደበኛ ወታደርና ባንዳ ጉጀሌ ጋር በቆራጥነት እየተጋፈጥን ነው።

 

ይህ ጦርነት የተነሳው እራሳችንን ስንጠብቅበት የኖረውን መሳሪያ ካልገፈፍን ብሎም አስረን ካላዋረድናቹህ ሲሉን ነው። በጎንደር ሕዝብ ላይ ድርብርብ ግፍ ሲያደርስ የኖረው ወያኔ የተፈጥሮ ድንበራችንን ተከዜን ተሻግሮ እስኪመለስ እንዲሁም ስልጣን ወደ ኢትዮጵያ ሕዝብ እስከሚመለስ ትግላችን ይቀጥላል።

ከህዳር 17 እስከ 24 2009 ቀናት ውስጥ በተደረጉት ከባድ ጦርነቶች በወያኔ ጦር ላይ ከህዝባችን ጋር ተቀናጅተን ከፍተኛ ድልን ተቀዳጅተናል። በአንድ የጦር ግንባር ብቻ እስካሁን እኛ የደረስንበትና ያረጋገጥነው የወያኔ ከባድ ጉዳት እንደሚከተለው ነው።

1. ኮሎኔል ይመር መለሰ አቡሃይ የተባለ የፀረ ሽምቅ ግብረ ሃይል ዋና አዛዥ ተገሏል።
2. ምክትል ሳጅን ዋጋየ ጫቅሉ በጦርነቱ ተገሏል።
3. 56 ወታደር ተደምስሷል።
4. 35 ቁስለኛና ቁጥራቸውን መግለፅ የማንፈልገው ብዛት ያላቸው በፍቃዳቸው ወያኔን ከድተው እጃቸውን የሰጡ አሉ።
5. መትረጌስ ከ260 ጥይት ጋር።
6. 56 ክላሽ ከነ ሙሉ ትጥቁ።

ይህ ግፈኛው ወያኔ እኛን ሆን ብሎ በርሃብ ለመፍጀት አመት ሙሉ የለፋንበትን ሰብላችንን በምንሰበሰብበት ወቅት መጥቶ መሳሪያ አውርዱ አለን። የጎንደር ሕዝብ ተነጥቀው የተወሰዱ የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት መሬቶች ይመለሱ እኛም ትግሬዎች አይደለንም ብለን በሰላም ብንጠይቅ ተወካዮቻችንን እንደሌባ በለሊት በትግሬ ኮማንዶ በከተማችን ጎንደር ላይ ማፈንን መረጡ።

ተው ብለን በአደባባይ በሰላም ጠየቅን። እነሱ ግን በእብሪት ጭራሽ ዘራችንን ሊያጠፉ ጦርነት ከፈቱብን። ይህ ተገደን የገባንበት ጦርነት ነው። ስለሆነም በቅርብ ያለው የደጋውም የቆላውም ወገራ ህዝብ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ እናቀርባለን። በጎጃምና በወሎ አልፎ የሚመጣውን ተጨማሪ የወያኔ ሃይል በያላቹህበት ግጠሙት። በተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል ህዝባዊ ቁጣው ተቀጣጥሎ ወያኔን በተቀናጀ መልኩ መደምሰስ አለብን።

በቅርብም በሩቅም ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ እራሳችንን መከላከል እንድንችል ሁለገብ ድጋፍ እንዲያደርግልን ይህን መልእክት ከጦር ሜዳ ልከናል።

በሰሜን ጎንደር ከቆላማው ወገራ የገበሬዎች ጎበዝ አለቃ አስተባባሪዎች:

ለጥንቅሩ ሙሉነህ ዮሃንስ

04356-barefoot2btplf2bsoldiers2b-2bethiopia

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: