ዶ/ር መረራ ጉዲና በአስቸኳይ እንዲለቀቁ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አንጋፋ አባል ጠየቁ

በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የውጭ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ አንጋፋ አባል ሴናተር ቤን ካርዲን በቅርቡ አዲስ አበባ ላይ የታሰሩት የተቃዋሚው የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግሬስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና እና ሌሎች በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ መሪዎችና ጋዜጠኞች እንዲለቀቁ የሚጠይቅ ጋዜጣዊ መግለጫ አወጡ።

የምክር ቤት አባሉ አክለውም፤ የኢትዮጵያ መንግስት በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችን፥ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትንና የሲቪል ማኅበረሰብ ታጋዮችንም እንዲፈታ፣ የፖለቲካ ምሕዳሩን ለማስፋት የሚያስችሉ ተጨባጭ እርምጃዎችን እንዲወስድና እንዲሁም በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን አገልግሎትና አቅርቦቶች ላይ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ፤ ሲሉ ጠይቀዋል።

የአውሮፓ ሕብረት ፓርላማ በጠራውና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ቀውስ ላይ ትኩረት ያደረገ ሥነ ሥርዓት የምስክርነት ቃል ከሰጡ በኋላ ባለፈው ሳምንት ወደ አገራቸው ሲመለሱ መታሰራቸውን የገለጸው የሴናተር ካርዲን ጋዜጣዊ መግለጫ “የዶ/ር መረራ ጉዲና እስር በመንግስቱ ላይ የሰላ ትችት የሚሰነዝሩ የፖሊቲካ ተቃዋሚ በመሆናቸው ብቻ ነው። በመሆኑም በአስቸኳይ መለቀቅ አለባቸው” ብለዋል።14956363_675774532577476_7196150966059779186_n

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: