የአፍሪካ ቀንድ የሳኡዲ ወታደራዊ ማእከል ሊቋቋምባት ነዉ

ሳኡዲ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አሰብን ለወታደራዊ መስፋፋትና መደራጀት ፍጆታቸዉ ሊያዉሉ መሆኑ መረጃዎች ይፋ ከሆኑ አንድ አመት በሗላ ሳኡዲ አረቢያ ጅቡቲ ዉስጥ ሌላ ወታደራዊ ማእከል ልታቋቁም ከስምምነት ላይ መደረሱ ታወቀ። የጅቡቲ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳኡዲ አረቢያ በጅቡቲ ዉስጥ ወታደራዊ ማእከል (Military Base) ማቋቋሟን አገራቸዉ በጽጋ እንደምትቀበለዉ አሳዉቀዋል ሲል አል አረቢያ ዘግቧል።
የሳኡዲ ወታደራዊ አመራሮችን ወሳኝ የሆኑ ቦታዎችን እንዳስጎበኙ የገለጹት የጅቡቲዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አገራቱ ይፋዊ የሆኑ ስምምነቶች ወደፊት እንደሚኖራቸዉ ጠቁመዋል። ጅቡቲ የአሜሪካንና የፈረንሳይን ወታደራዊ ማእከላት ያሉባት መሆኑ ይታወቃል።
ሳኡዲ አረቢያና ወታደራዊ አጋሮቿ በጅቡቲ ዉስጥ ወታደራዊ ተቋምን ለመገንባት ማሰባቸዉ በኢራን የሚደገፉትን የየመን የሁቲ አማጽያን የባህር ላይ ዝውዉር ለመግታት መሆኑ ተጠቁሟል። በተጨማሪም የሳኡዲ አረቢያ ጅቡቲ መዝለቋ በመልካአምድራዊ የፖለቲካና የዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች በምስራቅ አፍሪካ ያላትን ተጽእኖ ለማላቅ መሆኑን ተንታኞች ያስረዳሉ። የጅቡቲ ባለስልጣናት በበኩላቸዉ
ከኢራን ጋር ያላቸዉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ኢራን ዉስጥ የሳኡዲ ኤምባሲ መቃጠሉን ተከትሎ መቋረጡን እየገለጹ ሳኡዲ ጅብቲ ዉስጥ የምትገነባዉ ወታደራዊ ተቋም የሙስሊም አገራቱ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር አካል መሆኑን ሳይሸሽጉ ያስረዳሉ።
በሳኡዲ የሚመራዉ ጥምር የ37 የሙስሊም አገራት ጦር፤ ሽብር ፈጠራን ለመከላከል አሰብ ዉስጥ ወታደራዊ ተቋም ሊገነባ ነዉ የሚለዉን ዜና ተከትሎ የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማሪያም ደሳለኝ ሳኡዲ አረቢያ ላይ “የምትከፍለዉ ዋጋ ይኖራል!” በማለት መዛታቸዉ የሚዘነጋ አይደለም። ሆኖም ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማሪያም ደሳለኝ ባለፍዉ የአዉሮፕያዉያኑ ወር ወደ ሳኡዲ አረቢያ በመጓዝ ተማጽኖ በሚያስመስል መልኩ ኤርትራን አስመልክቶ አቤቱታ ማቅረባቸዉ ይታወሳል።
የሙስሊምናን የባህረ ሰላጤዉ አገራት በአፍሪካ ቀንድ ዉስጥ የሚያደርጉት ወታደራዊ መስፋፋት ያለዉ ጠቀሜታና ጉዳት በስፋት አልተተነተነም።ለአሁኑ የታወቀዉ ነገር ቢኖር ኤርትራና ጅቡቲ የ37 ጥምር የሙስሊም አገራት ጦር ተባባሪ መሆናቸዉ ነዉ።

Image result for saudi military power

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: