የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ወጣት እንደግ አዳነ በረሃ ወርዶ አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቀለ፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን ድረጅት ጉዳይ ኃላፊና የሟቹ ሳሙኤል አወቀ የቅርብ ጓደኛ እንዲሁም የትግል አጋር የነበረው ወጣት እንደግ አዳነ በ2007 ዓ.ም በተካሄደው የይስሙላህ ምርጫ ሞጣ ወረዳ ላይ ለተወካዮች ምክር ቤት የተወዳደረ ሲሆን አሁን ደግሞ የህወሓትን አገዛዝ ፈፅሞ በሰላማዊ ትግል መለወጥ እንደማይቻል አምኖ ጫካ ገብቶ ብረት አንስቷል፡፡
“ሰላማዊ ትግል አብቅቶለታል!” ሲልም ለአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ተናግሯል፡፡
ወጣት እንደግ አዳነ በ2007 ዓ.ም የሞጣ ወረዳን ወክሎ ለምርጫ በተወዳደረበት ወቅት የህወሓት አገዛዝ ማዳበሪያ በመከልከልና ሌላም የበቀል እርምጃ በመውሰድ በገበሬ ቤተሰቦቹ ላይ በደል እንዳደረሰ ገልጿል፡፡ በምርጫው ማግስት የሞጣ ህዝብ የሰጠውን ድምፅ በጠብመንጃ ከመነጠቁ በላይ የህወሓት ደህንነቶች አፍነውት ልብሶቹን አስወልቀው መለመላውን ብርድ ላይ አቁመው በማሳደር ሰቆቃ ፈፅመውበታል፡፡
አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቅሎ አሁን በረሃ ውስጥ የሚገኘው ወጣት እንደግ አዳነ “ከንቱ መሰዋዕትነት ከመክፈልና ጊዜ ከመፍጀት ውጭ ፈፅሞ ለውጥ ማምጣት ስለማይቻል ከተማ የቀራችሁ የሰላማዊ ትግል ጓዶቼ በሙሉ ፈጥናችሁ የእኔን ፈለግ እንድትከተሉና ትክክለኛውን የትግል አማራጭ እንድትይዙ፡፡” ሲል ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

Ethio Hagere's photo.Ethio Hagere's photo.
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: