በፌደራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ቦንብ ተገኝቷል በሚል ሰበብ በርካታ ፖሊሶች ታሰሩ

ኢሳት ዜና :- ከሶስት ቀናት በፊት ሜክሲኮ አደባባይ በሚገኘው በፌደራል ፖሊስ ዋናው ጽ/ቤት ወንጀል ምርመራ ክፍል ውስጥ ቦንብ ተገኝቷል በሚል ሰበብ በርካታ የኦሮሞና አማራ ተወላጅ ፖሊሶች ታሰረዋል።
ምንጮች እንደገለጹት ቦንቡ ሆን ተብሎ ፖሊሶችን ለማጥመድ ተብሎ በህወሃት የፌደራል ፖሊስ አባላትና የደህንነት ሰዎች የተቀነባባረ ነው። በወንጀል ምርምራ ክፍል ውስጥ የጦር መሳሪያ እንደማይገባ የሚገልጹት ምንጮች፣ ድርጊቱ አገዛዙን ይቃወማሉ ተብለው የሚታሰቡትን የሁለቱን ብሄር ተወላጅ ፖሊሶችን ለመወንጀል ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ይህንን ተከትሎ በእለቱ ተራኛ የነበሩ ዘበኞች ሳይቀሩ ታስረዋል።
ኢሳት የፌደራል ፖሊስ አባላት ውስጣዊ ተቃውሞ እያሰሙና ስራቸውንም እየለቀቁ መሆኑን ቀደም ብሎ መዘገቡ ይታወቃል። ነባር የኦሮሞና የአማራ ወንጀል ምርመራ ፖሊሶችን በማባረር በምትካቸው አዳዲስ አስልጠነው ያመጡዋቸውን ወጣት ምሩቃን እየቀጠሩ ነው።
በወንጀል ምርመራ ወቅት የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ተከሳሾች ጉዳይ በአማራ ተወላጅ መርማሪዎች፣ የአማራ ተወላጅ ተከሳሾችን ጉዳይ በኦሮሞ ተወላጅ መርማሪዎች እንዲታይ በማድረግ የሁለቱ ብሄር ተወላጅ ፖሊሶች እና ዜጎች እርስ በርስ እንዲጋጩ ሙከራ ሲደረግ መቆየቱንም ምንጮች አክለው ገልጸዋል።

13681996_10205098843029317_1398684269_o

 

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: