ሰሜን ጎንደር ግንባር…አዲስ የአጋዚ ሃይል ዳባት ገብቷል! ጥንቃቄ! ALERT our people and SHARE IT!

ስድስት ቀን በዘለቀው ጦርነት ወያኔ በቆላማው ወገራ በታጠቀው ገበሬ የደረሰበትን አይቀጡ ቅጣት ለመመከት ተጨማሪ ሃይል ወደቆላው ለመላክ ዳባት ላይ አዲስ የአጋዚ ሃይል አስፍሯል። ይህ ትናንት የገባው አጋዚ በስተሰሜን በደባርቅ በኩል እንደመጣ ታውቋል። ከትግራይ የመጣ ነው ተብሎ ይታመናል። በጎጃም መስመርም አዲስ ሃይል ወደዚህ አቅጣጫ እየተላከ ለመሆኑ መረጃወች አሁንም እየደረሱ ነው። ስለሆነም ለወገን ዘመድ ነቅቶ በር እንዲጠብቅ መልእክት ባስቸኳይ ይድረስ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ 6ተኛ ቀኑን በያዘው የቆላማው ወገራ ውጊያ ውጊያ ብዛት ያለው የአጋዚ ወታደር እንደቅጠል የረገፈበት አሳዥ ሻለቃ ሃይላይ ከዳባት ወረዳ የወያኔ ቅጥረኛ የፀጥታ ሃላፊ ሙሉየ ሹምየ በብስጭት እርስ በርስ እንደተታኮሱ ታውቋል። ምክንያቱም ቅጥረኛው ሙሉየ ወደቆላው ወታደሩን መርተህ ወስደህ ለእርድ ዳረክብኝ በማለት እንደተጣሉ መረጃ ደርሷል!

በበለሳና በአንዳንድ የደቡብ ጎንደር ቦታወች በወያኔ ላይ ጦርነት እንደተከፈተበት ታውቋል። እየተከታተልኩ ነው። የመተማና የቋራ ህዝብ ለወያኔ ሞት ደግሷል። በአርማጭሆ፣ በጠገዴና በወልቃይት ያለው የህዝብ ቁጣ ወያኔን እየለበለበው ነው። የጎንደር ህዝብ ከተቃጣበት አደጋ እራሱን ተከላክሎ እያጠቃ ነው። አስቸኳይ ሁለገብ ድጋፍ ግን ያስፈልገዋል። የመኸር እህሉን እንኳን ሳይከውን ነው ወያኔ በመሳሪያ ገፈፋ ሰበብ ጦርነት የከፈተችው።

በሌላ በኩል በኤርትራ ድንበር እየገፉ የመጡት የአርበኞች ግንቦት7 ሃይል ጦርነት ላይ መሆናቸውን ወያኔ ሳይቀር አምኖ ዜና እየሰራ ነው።

ስለሆነም የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ በቅርብ የሚገኘው የጎጃም የሰሜን ሽዋና የወሎ ክዝብ ልዩ የድጋፍ ጥሪ ከጎንደር የጎበዝ አለቆች ቀርቦለታል። ወገኑ ጎንደር ላይ ይህ ጦርነት ሲከፈትበት የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ዝም ብሎ ሊያየው አይገባም። ይህን መረጃ ለሁሉም በማዳረስ የቅስቀሳ ስራ ያስፈልጋል።

የከሌ አካባቢ አመፅ የዛ አካባቢ አብዮት የሚሉት ወገኖችም ባላለቀ አብዮት ላይ የመንግስት ምስረታ አተካሮ ከሚዳክሩ ወያኔን በህብረት በመጣል ለሁሉም እኩል የምትሆን ሃገር መመስረት ላይ ቢያተኩሩ ይሻላቸዋል። ምክር የምትችሉ ምከሩ…
ሙሉነህ ዮሃንስ

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: