የአማራና የኦሮሞ ስደተኞች ተለይተው ያለፍቃዳቸው ለወያኔ መንግስት በአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አማካኝነት ከጅቡቲ ተላልፈው ተሰጡ።

ስሙን መግለጽ ያልፈለገና ሁኔታውን ሲከታተል የነበረ በጅቡቲ የሚገኝ የአይን እማኝ ወደ 150 የሚደርሱ ስደተኞች ያለፍላጎታቸው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል በማለት ተናግሯል። እነዚህ ስደተኞች ከየመን በመርከብ ተጭነው በአለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት አማካኝነት ወደ ጅቡቲ ቢገቡም የወያኔ መንግስት የጅቡቲ መንግስትና የአለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት በመደዋወል በተለይ የአማራና የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን ያለፍቃዳቸው ወደ ኢትዮጵያ ቅዳሜ 17 ህዳር 2009ዓም በአውሮፕላን እንዲመለሱ ሲደረጉ አይቻለው በማለት ይህ የአይን እማኝ ምስክርነቱን ሰጥቷል።

የአለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት የጅቡቲ ተወካይ ሌሊ ቪዮሳኒ በበኩላቸው እነዚህ 150 ስደተኞች የተመለሱት ፍቃዳቸውን የሚገልጽ አስፈላጊውን ፎርም ሞልተውና ወደ አገራቸው መመለስ እንደሚፈልጉ ጠይቀው የተመለሱ ናቸው ብለዋል።

የአለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት የየመን ተወካይ ሻባ ሞአሊማን በዚሁ ጉዳይ ላይ ተጠይቀው ስደተኞቹ በፍቃዳቸው የተመለሱ እንጂ በፍጹም ተላልፈው የተሰጡ አይደሉም በማለት መልስ ሰጥተዋል። የቀድሞው ግንቦት ሰባት ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌ ከየመንርዕሠ ከተማ ሰነዓ አዉሮፕላን ማረፊያ ተይዘዉ በህገወጥ መንገድ ለወያኔ አገዛዝ ተላልፈው መሰጠታቸው ይታወሳል።

ወደ 150 የሚደርሱ ስደተኞቹም ከትግራይ ከአፋር ከአማራና ከኦሮሚያ ክልል የተሰደዱ መሆናቸውን የፍልሰተኛ ድርጅቱ የጅቡቲና የየመን ሃላፌዎች ገልጸዋል። ስደተኞቹ ወደ ጅቡቲ የገቡት መጠለያ ጣቢያ ገብተን ጉዳያችን ይታያል ብለው እንጂ ለወያኔ ተላልፈን እንሰጣለን ብለው እንዳልነበረ የአይን ምስክሩ አክሎ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግሯል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: