ሰበር ዜና። ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በአውሮፓ ህብረት ስብሰባ ከተሳተፉ በኋላ ዛሬ ወደ ሀገር ቤት ሲመለሱ ለእስር ተዳረጉ።

ላለፉት 25 አመታት በስላማዊ መንገድ ወያኔን እየታገሉ ካሉ ግንባር ቀደም ተጠቃሹ የዩኒቨርስቲ መምህሩ ዶክተር መራራ ጉዲና ከ አውሮፓ ህብረት በ ኢትዮጵያ በተቀሰቀሰው ህዝባዊ እምቢተኝነት እና አመፅ ዙሪያ መንግሥት እየወሰደ ባለው እርምጃ ጉዳይ ለይ ማብራሪያ እንዲሰጧቻው ተጠርተው በ ህብረቱ ጉባኤ ተገኝተው ገለፃ ማድረጋቻው የሚታወስ ሲሆን ።

እንዲሁም አውሮፓ ህብረት ለስብሰባ ጠርቷቸው የመጡትና ከተለያዩ ኢትዮጵያዊያ ጋር ህዝባዊ ስብሰባ ሲያደርጉ የነበሩት ዶክተር መራራ ጉዲና ዛሬ ወደ ሃገራቸው ሲመለሱ ከኤርፖርት ተይዘው መታሰራቸው ተሰምቷል ።

አንዳንድ ተነንተኞች እንዳስታወቁት በአዲሱ ኮማንድ ፖስት እና አዋጅ በመጣስ ሊከሰሱ እንደሚችሉ እያስታወቁ ሲሆን አዋጁ የዜጎችን የመንቀሳቀስ ,,,, የመናገር ብሎም ስብ አዊ መብት ይጋገፋል ሲሉ ሰበእዊ መብት ተሞጋቾች በተደጋጋሚ የኢትዮጵያን መንግስት ማሰገንዘባቻው እና ማስጠንቃቃቻው ይታውቋል አዋጁ ተግባራዊ ከሆነ ወዲህ በሺህ የሚቆጠሩ ዜጎቻችን ወደ እስር በገዢው መንግስት መታሰራቻው ይታወቃል ።

ድል ለሰፊው ለተጮቀነው ህዝብ !

14956363_675774532577476_7196150966059779186_n

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to ሰበር ዜና። ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በአውሮፓ ህብረት ስብሰባ ከተሳተፉ በኋላ ዛሬ ወደ ሀገር ቤት ሲመለሱ ለእስር ተዳረጉ።

 1. በለው! says:

  » ዶ/ር መረራም ሆነ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ጋር የተጋበዙት በአውሮፓ ሕብረት መሆኑን እያወቀ ሆን ብሎ ልማታዊ ወዶ ገብ ጋዜጠኛ ቢኒያም ከበደ ዶ/መራራ ጉዲና የኮማንድ ፖስቱ አንቀጽ 2. ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ማድረግ (1). በሽብር ከተሰየሙ ድርጅቶች እና ከጸረ ሰላም ቡድኖች ጋር ግንኙነት ማድረግ፡ የሚለውን በመጥቀስ “ቀይ መስመር አለፉ ሲል በቀይ ፅፏል።”
  >> ይህ የሚያሳይው የመረጃ መቀባበልን መሽቀዳደምን እንጂ ይህ አዋጅ ‘አስቸኳይ’ ከሚለው ቃለ አጋኖ በቀር የአሸባሪው ህግ ስለሆነ ለእሱ ብርቅ ሆኖበት ነው። እኔ የማደንቀው “የአውሮፓ ኮሚሽን የአሸባሪ ቡድን ጠርቶ ስላነጋገረ ጽ/ቤቱ ከሀገራችን በአስቸኳይ ይውጣ ንክኪ ያላቸውም ኤምባሲዎች ይዘጉ! ከዛሬም ጀምሮ ምንም ዕርዳታ እንዳትልኩብን ብሎ በጥቁር ቢጽፍ ጥሩ ነበር።
  **የኢህአዴግ ካድሬ፡ጋዜጣ በሎች፡ተደጋፊዎች፡አድርባዮች(አዜብ ጎላ እንዳሉት) የሚያቀነቀኑት “ዲያስፖራው ለድሃ ወገኑ የምግብ እርዳታ እንዲቆም ማድረጉ..ጸረ ሕዝብነት ነው።”ይላሉ በተጓዳኝ በምግብ እራሳችንን ችለናል…ከአፍሪካ አንደኛ..ከዓለም ሁለትኛ ተብለን የዓለም መንግስታት ፈነደቁ ይሉና…ርሃብ ሳይሆን የምግብ ዕጥረት ከ9-15ሚሊየን ሕዝብ ላይ ተከሰተ ብለው እህሉን ደፍተው ጆንያውን ሸጠው የኢኮኖሚ ኢምባየር የሚገነቡ ናቸው። ቢኒያም ከበደ ካናዳ ቀለም መቀየጥ እንጂ የህወአት የፖለቲካል ቅወጣና ቅየጣ አልገባውም ጭራሽም አይገባውም። ግን አንዳንዶች በሕገመንግስታዊ (ማኒፌስቶ) ጥቅማጥቅማችን ካልተተገበረ ለንብረት መውደምም፡ ለግልበጣም፡ መሐላችሁ ገብተናል እናፈርሳልን!..እንበታትናለን! ሲሉ ምነው ድምጻቸው አልተሰማ?ይህ መፈክርና ቻርተር በነጭ መስመር ጉዞ ሆኖ ነው? አረንጓዴ ይለፍ ተሰጥቶት? ወይንስ የራሱ የታላቁ መሪና የአስቸኳይ አዋጁ ራዕይ ስለሆነ!? ታዘብኩሽ አለ እንዲህ ብስ ስ ስ ስ ስትል ሳይሰማት..ይሁን እስቲ። November 13, 2016
  ********************!
  »…” የታሪክ ሂሳብ ማወራረዱን አቁሙ!” መራራ ጉዲና….” በቁጥጥር ሥር ዋሉ!”
  ___በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው የታሪክ ቁርሾ እንዲቀጥል የሚፈልገው ቡድንና ኅይል ነውን? ምንም እንኳ የሽብርተኛ አዋጁ አብሮ የተቀመጠ፡ ሻይ ቡና ያለ ቢልም …የአስቸኳይ (የችኮላና የችከላ) አዋጁ ግን ስድስት ወር ለብሔር በሔረሰቦች ደህንነት ሲባል ብሔር ብሔረሰቦች..እንዳይናገሩ..እንዳየፅፉ…ዓይነ ስውራን እንኳ ቢሆኑ በምልክት እራሳቸውን እንዳይገልጹ …ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ እንዳይከፍቱ የሚከለክል..ሕገ ጠርንፍ ሲታወጅ ለሕዝቦች (ለውጭ ዜጎችና ልዩ ልዩ ጥቅማጥቀም ላላቸው ከ፳፭ ኪሎ.ሜ ወጭ እንዳይጓዙ የሚለውን ዕገዳ ሲዘርዝ ሌላውን በብሔር ብሔረሰቦች አጠናክሮ ቀጥሏል። አንዳንዶችም ቀጥልበት ሲሉ ሌሎች የጥረነፋውን የችኮላ አዋጅ አሳጥረን የሚመጣው ይታይ ብለው የሚያደፋፍሩም አሉ።
  ___በዚህ አጋጣሚ ህወአት/የኢህአዴግ ጥልቅ ተሃደሶ ምስክር የሚሆነው ለመጀመሪያ ግዜ ሰው ከሀገሩ ሲከዳ የአዕምሮ በሽተኛ ነው ብሎ ሰው ነጻ ሳያደረግ፡ ጭራሽ በዓለም ፊት የተቃወመን ስፖርተኛ ሌሊሳ ፈይሳን “ጀግናችን ነው የጀግና አቀባበል እናደርግለታለን ኢህአዴግ ደሞክራሲያዊ ነው ተቃወሞ ይደግፋል ያበረታታል” ብሎ ነበር።
  ____ አሁን መራራ ጉዲናን ሲያስር “የጀግና አቀባበል ይህን እንደሚመስል ሕዝብ ለአለም ስብሰባውን ለመሩት ማሰተዋወቁ ነው? በመራራ መታሰር ሌሊሳ ፈይሳ ነፃ ወጣ በለው! ምን አልባትም በአዲሱ ጥልቅና ምጥቅ የምሁራን ካቢኔ ተሃደሶ…የወርቅነህ ገበየሁ ነገዎ (ገበየሁ) ሥምና ክብር ማጉደፍ የኦሮሞ ዜግነት ለኤርትራዊው ለተስፋዬ ግብረእባብ (ገዳ) የተሰጠ ለምን ለትግሬው ወርቅነህ ገበየሁ (ነገዎ) ይከለከላል?።
  ** ችግራችን ጀመረ እንጂ አላለቀም እንዳይጨርሰን እንጠቀቅ!…በመፈቃቀርና በመፈቃቀድ ፹ ከመቶ የኢትዮጵያ ሕዝብ(ገበሬ)የህወአት/ኢህአዴግ የግል ንብረቴ ነው ብሎ በረከት ስምኦን ከነገረን.. ሶስተኛ አማራጭ ፓርቲ (በመደናነቅና በመሞጋግስ) ልደቱ አያሌው አሁን (ጠንካራ ተፎካካሪ) አዲስ ፓርቲም የመፍጠሩን ከወዲሁ “ሚዲያው በቡዳ በልቶት” ሌት ተቀን ያስጓራዋል ። የቸኮለው አዋጅ ራዕይ ወደታች ለማስረጽ፡ አዲስ በጥልቀት ለነውጥ ማበረታታት እንጂ ለውጥ ተስፋ የለውም!! አንገት አልባ እራስ በለው!! በቸር ይግጠመን

  Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: