በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራው የአማራ ክልላዊ መንግስት የክልሉን ወጣቶች እያባበለ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራው የአማራ ክልላዊ መንግስት የክልሉን ወጣቶች እያባበለ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ በክልሉ ካለው ውጥረት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ድንጋጤ ላይ የወደቀው የክልሉ አስተዳደር፣ በተለይም ታጣቂው አርሶ አደር ከመንግስት ጋር ይፋ ጦርነት መጀመሩ በእጅጉ ረብሾታል ተብሏል፡፡ እንደ መረጃዎች ገለጻ ከሆነ፣ ክልሉን የሚያስተዳድረው የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ካቢኔ፣ ልቡ ለለውጥ የሸፈተውን ነዋሪ በገንዘብ ጭምር የመደለል ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡
ከዚህ ቀደም በክልሉ የብድር ጥያቄ ያቀርቡ የነበሩ ወጣቶች ጥያቄአቸው አፋጣኝ ምላሽ ካለማግኘቱም በላይ፣ በቂ ዋስ አላቀረባችሁም በሚል ምክንያት ብዙ መጉላላት ይደርስባቸው እንደነበር የአስተዳደሩን በሙስና የተጨማለቀ አሰራር ዋቢ ያደረጉ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ አሁን ግን የአማራ ክልል ህዝብ በተለይም ወጣቱ የለውጥ አብዮት ማቀንቀኑን ተከትሎ፣ የክልሉ አስተዳደር የስራ ፕሮፖዛል ለሚያቀርቡ ወጣቶች ያለ ምንም ዋስትና ገንዘብ ለመልቀቅ መወሰኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ይህም ለውጥ ፈላጊው ህዝብ በአስተዳደሩ ላይ የፈጠረው ተፅዕኖ እንደሆነ ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡
የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) እንደማይወክለው በተደጋጋሚ ሲገልጽ የሚደመጠው የክልሉ ህዝብ፣ በብአዴን ጋሻ ጃግሬነት በህወሓት ያጣውን ነጻነቱን ለማስመለስ ከሰላማዊ ትግል ጀምሮ የትጥቅ ትግልን ያካተተ የለውጥ አብዮት እያካሔደ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ የአማራ ክልልን የሚያስተዳድረው ብአዴን፣ ወጣቱ በክልሉ እያካሔደ ያለውን ህዝባዊ አብዮት ለመቀልበስ በሚመስል መልኩ፣ ለስራ ፈጠራ በሚል ሰበብ ከዚህ በፊት አድርጎት የማያውቀውን የ2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በጀት መመደቡንም መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

BBN

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: