የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት በወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ኢትዮጵያንና ኢትዮጲያዊነትን ለማዳን ብሎም የተጨቆነውን ህዝባችንን በጫንቃው ላይ የተጫነበትን የባርነት ቀንበር አሽቀንጥሮ በመጣል ህዝብ ቀና ብሎ እንዲሄድና የዴሞክራሲ ተጠቃሚ እንዲሆን መራራና እልህ አስጨራሽ የትጥቅ ትግል እያካሄደ የሚገኘው ጀግናው የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ከወያኔው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሃይልና መከላከያ ሰራዊት ጋር ባደረገው ተከታታይ የማጥቃት እርምጃ የወያኔን ሹማምንቶች አንገት ያስደፋ አንፀባራቂ ድል ማስመዝገቡን አርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን ከስፍራ ባደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ህዳር 16 ቀን 2009 ዓ.ም. የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በወያኔው አወቃቀር ክልል 3 ብሎ በሚጠራው አካባቢ ግጨው በተባለው ቦታ ከወያኔ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሃይል ጋር ባደረገው እረጅም ሰዓት የፈጀ ውጊያ 22 በመግደልና 29 ደግሞ በማቁሰል በጠላት ላይ ወታደራዊ የበላይነትን የተቀዳጀ ሲሆን የወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሃይል የቆሰሉ ወታደሮችም ዲቪዥን ወደሚገኘው ሆስፒታል እንደተጓጓዙም የሪፖርተራችን መረጃ ገልጿል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለም ህዳር 17 ቀን 2009 ዓ.ም. በዚሁ በአማራ ክልል ዳንሻ አካባቢ ልዩ ስሙ ማይለሚን በተባለው ቦታ የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ከወያኔው የመከላከያ ሰራዊት ጋር ባደረገው ውጊያ 12 በመግደልና 14 በማቁሰል የወያኔን አምባገነናዊ አገዛዝ ሹማምንቶችን ቅስማቸውን የሰበረ አንፀባራቂ ድል እንዲሁም የወገንን አንጀት ያራሰ ድል መጎናፀፉን የአርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን አክሎ ገልጿል፡፡
በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች የህብረተሰቡን ድጋፍ እያገኘና ህዝብን ከጎኑ ማሰለፍ የቻለው የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ባደረጋቸው ተከታታይ እልህ አስጨራሽ ውጊያዎች የሃገርና የወገን ደራሽነቱን ያስመሰከረበትን ከፍተኛ ድል ማስመዝገቡንና ይዞት የተነሳው አላማም በሃገራችን ላይ የተንሰራፋውን አምባገነናዊ ስርዓት ገርስሶ በመጣል ሃገርና ህዝብን መታደግ በመሆኑ የአካባቢ ነዋሪ ማህበረሰብም ከፍተኛ አቀባበልና ድጋፍ እያደረገለት ይገኛል፡፡

Image may contain: text, outdoor and one or more people
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

3 Responses to የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት በወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

 1. Tizita Geletaw says:

  Wey tamir!
  Asegid’s ‘news’ is misinformation, which helps only woyane. This is a white lie, with no credibility at all. G7 has no single fighter on the ground. period.
  please, let us save this country by telling the truth. The truth is there is some armed struggle in Gondar, but this armed struggle is done by the people led by their own gobez aleqa. let us support the good cause for our people and country. let us stop fabricating lies like woyane. some are paid to report lies.

  Like

 2. mekonnen shalamo says:

  ማፈረም የለም መደመሰሱንም አለሰማም ዉሸት ነዉሪ ነዉ የምያምን የላቸዉሙ.’.

  2016-11-28 13:20 GMT+03:00 Freedom4Ethiopian :

  > Aseged Tamene posted: “ኢትዮጵያንና ኢትዮጲያዊነትን ለማዳን ብሎም የተጨቆነውን ህዝባችንን በጫንቃው ላይ
  > የተጫነበትን የባርነት ቀንበር አሽቀንጥሮ በመጣል ህዝብ ቀና ብሎ እንዲሄድና የዴሞክራሲ ተጠቃሚ እንዲሆን መራራና እልህ
  > አስጨራሽ የትጥቅ ትግል እያካሄደ የሚገኘው ጀግናው የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ከወያኔው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ
  > ፖስት ግብረ ሃይልና መከላከያ ሰራዊት ጋር ባደረገው ተከታታይ የማጥቃት እርምጃ የወያ”
  >

  Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: