የብሪታንያ መንግስት የሀገሩ ዜጎች ወደ አማራ ክልል እንዳይሔዱ አስጠነቀቀ

በአማራ ክልል በመንግስት ወታደሮች እና በታጣቂ ኃይሎች መካከል የሚደረገው ውጊያ መቀጠሉ ታውቋል፡፡ ራሳቸውን ያደራጁ የህዝብ ወገኖች በመንግስት በተለይም በህወሓቱ አጋዚ ወታደሮች ላይ እያደረሱ ያሉት ጥቃት መንግስትን ዋጋ እያስከፈለው ይገኛል ተብሏል፡፡ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የሚደረገው ውጊያም የፌደራሉን ጨምሮ የክልሉን መንግስት ስጋት ላይ እደጣላቸው የመረጃ ምንጮች አመላክተዋል፡፡

እንደ መረጃዎች ገለጻ ከሆነ፣ በአርማጭሆ ውስጥ ሳንጃ በተባለ ወረዳ ከፍተኛ ውጥረት የነገሰ ሲሆን፣ በስፍራውም የመንግስት ታጣቂዎች በተጠንቀቅ መቆማቸው ተነግሯል፡፡ በሰሜን ጎንደር አካባቢ የተደራጀው ህዝባዊ እና ታጣቂ ኃይል በመንግስት ላይ መሸፈቱን ተከትሎ፣ አካባቢው መረጋጋት ርቆታል ተብሏል፡፡ እንደ ሁመራ፣ ቃብትያ እና አብደራፊ ያሉ የአማራ ክልል አካባቢዎች መደበኛ የውጊያ አውድማ እየሆኑ መምጣታቸውን ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የብሪታንያ መንግስት የሀገሩ ዜጎች ወደ አማራ ክልል እንዳይሔዱ አስጠንቅቋል፡፡ ለወሳኝ ጉዳይ ካልሆነ በቀር ዜጎቹ ወደ ክልሉ እዳይሔዱ ያስጠነቀቀው የብሪታንያ መንግስት ባወጣው መግለጫም ዜጎቹ ምስራቅ ጎጃም፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ጎንደር፣ ደቡብ ጎንደር እና ባህርዳር ወደተባሉት የአማራ ክልል ስፍራዎች እንዳይሔዱ ዜጎቹን አስጠንቅቋል፡፡ የብሪታንያ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዜጎቹ የማስጠንቀቂያ መግለጫ ያወጣው ትላንት ረቡዕ ነው፡፡ የብሪታንያ መንግስት መግለጫውን ሊያወጣ የቻለው፣ በአማራ ክልል በመንግስት እና ራሳቸውን ባደራጁ ህዝባዊ ኃይሎች መካከል እየተካሔደ ያለውን ውጊያ ተከትሎ እንደሆነ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

 

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: