በአርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል

ጎንደር ከተማ የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በአርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ረቡዕ ዕለት አንድ የጭነት መኪና በተወሰደበት ዕርምጃ መቃጠሉንም የአይን ዕማኞች ገልጸዋል።
በተበታተነ መልኩ ሲካሄዱ የነበሩ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች በአንድ ዕዝ በተቀናጀ መንገድ እንዲካሄዱ ስምምነት ላይ መደረሱንም በበረሃ የሚገኙት ታጣቂዎች ከኢሳት ጋር ባካሄዱት ቃለ-ምልልስ ገልጸዋል።
በሰሜን ኢትዮጵያ በአማራ ክልል በተለይም በሰሜን ጎንደር በየአካባቢው ተደራጅተው በጎበዝ አለቆች እየተመሩ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ሃይሎች በጋራና በአንድ ዕዝ ስር ለመታገል መወሰናቸውንና በቤተክርስቲያን ተገኝተው ቃል መሃላ መፈጸማቸውን ለኢሳት አስታውቀዋል።
ሰኞ ህዳር 12 / 2009 ዓም በአንድነት ሆነው በጋራ ዕዝ ለመታገል የወሰኑት በቁጥር 450 የሚሆኑ ታጣቂዎች ኢትዮጵያ ነጻነቷን እስከምታገኝ እንደሚታገሉ አረጋግጠዋል።
በሰሜንና ደቡብ ጎንደር ቴዎድሮስ በሚል ስያሜ በሁለት ቡድን የተከፈሉት የታጠቁ ሃይሎች ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩም የእንቅስቃሴው መሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ከአርበኞች ግንቦት 7 የተጠናከረ ድጋፍ እንደሚፈልጉም ነው የተናገሩት።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰሜን ኢትዮጵያ የቀጠለው የትጥቅ ትግል በአብደራፊ፣ ቃብትያና፣ ሁመራ አካባቢዎች ተጠናክሮ መቀጠሉን የሚገልጹት የአይን ምስክሮች የታጠቁ ሃይሎች ረቡዕ ዕለት በሳንጃ ወረዳ በሰነዘሩት ጥቃት የዳሽን ቢራ የጫነ መኪና መቃጠሉን ገልጸዋል።
በዚህም ጥቃት ሳቢያ መንገድ በመዘጋቱ በርካታ መኪኖች ከእንቅስቃሴ መገታታቸው ታውቋል።
ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በአብደራፊ እና በቃፍቲያ ወታደራዊ ግጭቶች መቀጠላቸው የተሰማ ሲሆን፣ በርካታ የታጠቁና ያልታጠቁ ሃይሎች ወደ ትግል መውጣት መጀመራቸው ተመልክቷል።

15123252_226347067794606_1099607009416258927_o

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: