ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የተሰጠ መግለጫ”ለጊዜው የመሸግንበትን ቦታ ወያኔ/ኢሕአዴግ በሄሊኮፕተር ቢደበድብም ሰራዊታችን መክቷቸዋል”

ህዳር 10/2009 ዓ.ም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተላለፈ ጥሪ በሃገራችን ኢትዮጵያ የወያኔ ኢሃዴግ ዘረኛን መንግስት ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነቅሎ ለመጣል እንደ መስቀል ችቦ በአራቱም መአዘናት ተቀጣጥሎ የሚገኘው የነጻነት ትግል ቀና ብሎ መጓዝን አሃዱ በማለት ጀምሯል። የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ባሳለፍነው ሳምንት ወስጥ በአደባይ፣በሃከር፣ ቀፍታና ሁመራ አካባቢ ከህዝብ ጠላትና ዘረኛ ስረዓት አራማጅ ከሆነው የወያኔ ኢሃዴግ ሰራዊት ጋር ባካሂደው ወጊያ በርካታ ድሎችን ማስመዝገቡና ወጤታማ የሆነበትን የአዲጎሽ ከተማን ህዝብ በማስባሰብ ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ በማድረግ ምላሽ አግኝቷል።

ምንም እንኳን ሰራዊታችን ለጊዜው መሽጎበት የነበረውን ከፍታ ነጥብ ቦታ የወያኔ /ኢሃዴግ ሰራዊት በከባድ መሳሪያ እና በሂሊኮፕተር በመታገዝ የሰነዘረውን ድንገተኛ ጥቃት በመመከትና የአካባቢውን ህዝብ በማስተባበር የአጠፊታ እርምጃ ወስዷል።

በተጨማሪም በታችኛው አርማጭሆ ፣አብርሃጅራን ጨምሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በተጓዘባቸው ቦታዎች የስረዓቱን አገልጋዮች በመቅጣት በገውላ እና ቀፍታ አጽመ-ሃርማዝ የሚገኘውን የወያኔን ሰራዊት በተለያዩ አቅጣጫዎች በመክበብ ከፍተኛ ውጊያ አካሂዷል። የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በተጓዘባቸው ስፍራዎች ከህዝቡ የተሰጠው ምላሽ እጅግ አስደሳችና የሃገር ፍቅር ስሜት የታየበት ታሪካዊና የማይረሳ ጊዜ ነበር።

በተጨማሪም ከመሰል የአካባቢው ታጣቂዎችና ለነጻነት የሚታገሉ አጋሮቹ ጋር ኩታ ለኩታ በመቋጠር መጪውን ሳምንት ለተሻለ ስራ የተለያዩ ዕቅድችንም እያወጣ ይገኛል። ስለሆነም በሌሎች ክልሎች የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ፣ የዚህን ግፈኛ ስረዓት ያለምትክ በማስቀረት የወደፊቷን ኢትዮጵያን ነጻና የሁሉም ዜጋ እኩል ምድር እንድትሆን የመታገያው ጊዜ አሁን ነው። በመሆኑም ሃገሪን ፣ወገኔን የምትል የዚህ ዘመን አደራ ያለብህ ትውልድ ፣ የምትነሳበት ጊዜ አሁን ነው !! የሃገርን ጉዳይ ዘር፣ቀለም፣ቦታና ሃይማኖት አይለዩትም !! ዛሬ ነገ ሳትል ተነስ ፣ታጠቅ እኛን ወንድሞችህን ፣እህቶችህን ምሰል በማለት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ::
አንድነት ሃይል ነው
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር

 
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የተሰጠ መግለጫ”ለጊዜው የመሸግንበትን ቦታ ወያኔ/ኢሕአዴግ በሄሊኮፕተር ቢደበድብም ሰራዊታችን መክቷቸዋል”

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: