በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ተቃውሞ እያሰሙ መሆኑን መረጃዎች ጠቆሙ፡፡

በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ተቃውሞ እያሰሙ መሆኑን መረጃዎች ጠቆሙ፡፡ በትላንትናው ምሽት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ ማካሔዳቸውን መረጃዎች የጠቆሙ ሲሆን፣ ተቃውሞ የተካሔደውም በዩኒቨርሲቲው አዋሮ ካምፓስ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህም የተነሳ ዛሬም ድረስ በጊቢው መረጋጋት እንደሌለ የጠቀሱት ምንጮች፣ በዩኒቨርሲቲው ጊቢ እና ከግቢው ውጭ የአጋዚ ወታደሮች ታጥቀው መሰማራታቸውን የዓይን እማኞች ገልጸዋል፡፡
በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ለተቀሰቀሰው የተማሪዎች ተቃውሞ ዋነኛ ምክንያት የሆነው አስቀድሞ በግቢው አካባቢ የተሰማሩት የአጋዚ ወታደሮች፣ ሰበብ እየፈለጉ በተማሪዎች ላይ የሚወስዱት የኃይል እርምጃ እየተባባሰ መምጣቱ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ በትላንቱ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተቃውሞም ቁጥራቸው ያልተገለጸ ተማሪዎች በአጋዚዎች የተጎዱ ሲሆን፣ ከተጎዱት ተማሪዎች መካከልም ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ እንዳሉ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
በተያያዘ ዜና፤ በወለጋ ዩኒቨርሲቲም በተመሳሳይ ሁኔታ ተቃውሞ መቀስቀሱን መረጃዎች አመላክተዋል፡፡ በትላንትናው ዕለት በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የተቀሰቀሰውን የተማሪዎች ተቃውሞ ተከትሎም በስፍራው የተሰማሩት የአጋዚ ወታደሮች ተኩስ ከፍተው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተቃውሞዉ የተነሳም በወታደሮች ተይዘው የተወሰዱ ተማሪዎች መኖራቸውን ከስፍራው የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡ በትላንትናው ዕለት በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተቃውሞ መቀስቀሱን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: