ሀገራችን ከገባችበት ችግር ለማዉጣት ብቸኛዉ አማራጭ የትጥቅ ትግልን ማፋፋም ነዉ ::

ታጋይ ጌትነት አናጋዉ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ አመራር ሀገራችን ከገባችበት አዘቅት ዉስጥ ለማዉጣት ህዝቡ እና በሀገርዉስጥም ሆነ በዉጭ ሀገር የሚኖሩ በሰላማዊ መንገድ ስርአቱን እንቀይራለን ብለዉ ይንቀሳቀሱ የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዋች ሰፊ እንቅስቃሴ ድፍን 24 አመት ሲይደርጉ ቆይተዋል ነገር ግን ይህ ትግል ገዥዉ ቡድን ካለዉ ባህሪ አንፃር እራሱን ወያኔን ሲያጠናክር እና እንደ እስስት መልኩን እየቀየረ የብዝበዛ እና የእስራት እንዲሁም ግድያዉ ተጠናቅሮ የቀጠለበት ሁኔታ ነዉ ያለዉ፤ አሁን ይህን ሁኔታ ህዝባችን እየገባዉ የመጣ ይመስላል ስለሆነም ወጣቱ የትጥቅ ትግሉን ወደ እሚያደርጉ ድርጅቶች እየተቀላቀለ ይገኛል። ነገርግን አሁንም ከማህበረሰባችን ዉስጥ የትጥቅ ትግሉን አያስፈልግም የሚሉ አስተያየቶች ይሰጣሉ እነዚህ አስተያየቶች ከየት እና ከማን እንደሚሰጥ ትግሉን ከሚያደርጉ እና ከኢትዮጵያ ህዝብ እይታ ዉጭ አደለም። ይህን አስተያየት ለመስጠት ይልቅ የትግል አማራጭ መስጠት ወይም ማቅረብ አስፈላጊ ነበር። ነገር ግን ይህን አስተያየት ከመስጠት ያለፈ የለም እንዳይቀመጥ ቀስቅሰዉ እንዳይሮጥ ደንግረዉ አይነት ነገር ነዉ። አወ ጦርነት ዘግናኝ ነዉ ጦርነት አዉዳሚ ነዉ የጦርነት አስከፊነትን ከአኛ ኢትዮጵያዉያን በላይ የሚያዉቅ የለም የጦርነት አስከፊነት ጠንቅቀን እናዉቃለን፤ የጦርነት አስከፊነትን ወያኔም ሊነግረን ይሞክራል፤ አወ አስከፊ ነዉ ነገር ግን ወደ ጦርነት እንድንገባ ወያኔ ገፍቶናል፤ ይህ እንዳይሆን በሰላማዊ መንገድ ስንታገል ይህ ጥሩ አደለም ብለን ነግረነዉ መልሱ ምን ሆነ እስራት፣ ማፈናቀል፣ከመንግስት ስራ ማባረር ሆነ እጣ ፈንታችን፤ ለዚያም ወደ ማንፈልገዉ መስመር ገብተናል። ጦርነት ሁሉንም ወገን እንደሚጎደ ጠንቅቀን እናዉቃለን፤ ሰዉ ሰዉነዉና እንደከብት ዝም ብሎ አይገዛም ክብሩን እና ሀገሩን እሚወድ የሀገሩ እና የወገኑ ክብር እምቢ ማለት አለበት፤ ሰዉ ሰዉ በ መሆኑ ብቻ መብቱ ሊከበርለት ይገባዋል። በባርነት ጥላ ስር መኖር የለበትም ባርነትን በአርነት፣ በእንቢተኝነት ማስወገድ አለበት ጭቆና ለመረረዉ ሰዉ የጦርነት አስከፊነትን አይምከሩ ጭቆና እምቢተኝነትን፣ጦርነትን ይወልዳልና፤ የጦርነት አስከፊነትን የሚነግሩን የጨቆኞች ደጋፊወችም ሆኑ አንዳንድ የዋሆች እሄን መገንዘብ አለባቸዉ፤ በተለይ የዋሆች ሳታዉቁም ይሁን አዉቃችሁ ጨቆኞችን እየደገፋችሁ እንደሆነ ልታዉቁ ይገባል ሳታዉቁ ከሆነ የምትተቹት ህዝቡ ወደ ትግሉ እንዲቀላቀል መደገፋ እና መርዳት ይኖርባችሃል። የትጥቅ ትግሉን የሚያደርጉ ግለሰቦች ለራሳቸዉ ሳይሆን ለሀገርና ለወገን እራሳቸዉን መስዋት እያረጉ ነዉ፤ ሌላ አላማ የላቸዉም ለሌላ አላማ ዉድ ህይወቱን እንደማይሰዋ ሊታወቅ ይገባል። የትጥቅ ትግሉን እንደሚያዋጣ ያመነ ትግሉን ይደግፍ ይርዳ ሌላዉ የዋሁ አስተያየት ከመስጠት ቢቆጠብ ጥሩ ነዉ እላለሁ። የሚደረገዉን የትጥቅ ትግል ኢትዮጵያን ይጎዳል ይላሉ አወ ይጎዳል ነገር ግን ጉዳቱ ከሀገር እና ከወገን ክብር እንዲሁም ከወያኔ ጭቆና አይበልጥም ነዉ እምንለዉ እኛ ከዚህ ይበልጣል የምትሉን ካላችሁ አሳዩን ካለያ ትግሉን ላለማቀጨጭ የዋሆች ዝምበሉ። ሌላዉ የትጥቅ ትግሉን አካሄድ ከመገንዘብም ይሁን ሳይገነዘቡ ታጋዮችን የተለያየ ትችት ይተቻሉ ወያኔን ያህል ትልቅ የሀገር እና የወገን ጠላት አስቀምጠን ሌላ ችግር ዉስጥ ገብተን እንድንፈተፍት ይተቹና፣ አስተያየት ይሰጡናል እዉነቴነዉ አሁንም ደግሜ እናገራለሁ ለኢትዮጵያ እና ህዝቧ ከወያኔ በላይ ጠላት አለ የሚል ካለ ሊያሳዩን ሊያስረዱን ይገባል ያልታየንን ለማየት ዝግጁ ነን፤ ለትግሉ እሚጠቅም ከሆነ። አለያ ግን ምንም አስተዋፆ ሳያደርጉ ዉድ ህይወታቸዉን ለሀገር እና ለወገን መሰዋት እያደረጉ ያሉ ታጋዮችን ባትተቹ ይሻላል ብትችሉ ደግፉ። እዉነቴን ነዉ የምናገረዉ አማራዉ በወለጋ፣ መተከል፣አሩሲ፣ሀረር፣ወልቃይት፣ጠለምት፣ፀገዴ እንዲሁም በሌሎች አካባቢ ተፈናቅላል፣ተሰዳል፣ሞቶአል፣ የዘር ማፅዳት እና ማጥፋት ተደርጎብናል አወ ይህንም በመገንዘብ ወገናችን ለማዳን የትጥቅ ትግል እያካሄድን እንገኛለን ለህዝባችንም አለን እያልነዉ ከጎኑ ሆነን መሰዋትነትን እየከፈልን እንገኛለን፤ እስኪ ማን ይሙት ከዚህ ሁሉ አማራን ያፈናቀለዉ ትልቁ ጠላት የኦሮሞዉ፣የጉምዙ፣የደቡቡ፣የጋምቤላዉ ህዝብ ነዉ ወይስ ወያኔና የወያኔ ሆድ አደር ካድሪዋች ናቸዉ፤እዉን ደቡብ ላይ አማራዉን ወያኔዋችሲያፈናቅሉ ህዝቡ ገንዘብ እና እህል አልሰጠም ፣ መተከል የወንበራ አና የባሩዳ ህዝብ እያለቀሰ ከአማራዉ ጎን አልቆመም፤ ወገኔ ትልቁን ጠላት አስቀምጠን ከሌላዉ ጋር አንተኩስ። ከፖለቲካዉ አቋም እና ከአማራዉ ጋ ካለቸዉ ጥላቻ የወያኔ ጋሻ ጃግሪ ሆኖ ኦነግ በሀረር፣አሩሲ እና ሌሎች ከካባቢዋች ዉድ ወገኖቻችን ሰዉቶአል ጨፍጭፋል፤ ነገር ግን አሁን ካለዉ አቋም አንፃር ሲታይ ከወያኔ የሚበልጥ ጠላት ነዉ እንዴ ለእኔ አይታየኝም፤ ስለዚህ ጠላቶቻችንን ለይተን እወቅ እላለሁ እኔ ይመስለኛል ትግሉን የሚተቹ አዛኝ ቅቤ አንጋች እንዳይሆንባችሁ ከቻላችሁ ታገሉ አለያ አርፋችሁ ተቀመጡ። አንዲት ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ! የአማራ ህዝብ ትግል
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: