አርበኞች ግንቦት ሰባት ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ ስልጠና መስጠት ጀመረ ።

ሰሜን ጎንደር የነጻነት ተጋድሎው ተጠናክሮ መቀጠሉ እየተሰማ ነው፥ ወያኔ ጉድ ፈላብሽ፥ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሰራዊት የሰሜን በሮችን እየሰበረ፥ ከአማራ የማንነት ጥያቄ ታጋዮችና ከአገር ውስጥ አርበኞች ጋር እየተቀላቀለ ነው።

የአማራ የማንነት ጥያቄን አንግቦ፥ ለመብቱና ለነጻነቱ ለመታገል ዱር ቤቴ ያለው የጎንደር ጀግና፥ የአርበኞች ግንቦት 7 የነጻነት ኃይሎችን እጆቹን ዘርግቶ መቀበሉንና በአንድነት ተሰልፎ ወያኔን እንደሚመታ በደስታ እያወጀ ነው፥

ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ሰብሮ የገባው የአርበኞች ግንቦት7 አብሪ ሰራዊት፥ በኢትዮጵያ ውስጥ ቦታ ተቆጣጥሮ ስልጠና መስጠት መጀመሩም ተገልጿል።

ከአርበኞች ግንቦት7 ንቅናቄ ወታደራዊ ክፍል የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ባለፉት ሳምንታት ታጣቂዎች በቃፍቲያ ሁመራ፣ አዲ ጎሹና አርማጭሆ አካባቢዎች እስከ እንቃሽ ድረስ ከህወሃት ኢህአዴግ ቃኝ ወታደሮች ጋር ተከታታይ የተኩስ ልውውጦችን አድርገዋል።

የነጻነት ተጋድሎውን ካህናትና መነኮሳትን ጨምሮ፥ እሴቱና ወንዱ፥ አዛውንቱና ወጣቱ፥ ከሊቅ እስከ ደቂቅ፥ እየተቀላቀለው መሆኑን ንቅናቄው በመግለጽ ላይ ነው።

ሞት ለወያኔ ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ፥ እንግዲ ምን ትሉ

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: