አቶ ሬድዋን ሁሴን “አህያውን ፈርቶ..

አቶ ሬድዋን ሁሴን ሚኒስትር ተደርገው እንደተሾሙ ቅድሚያ ያመሩት ወደኦሎምፒክ ኮሚቴ አካባቢ ነበር። ምክንያቱ አንድ ቀድሞ የደረሳቸው ጥቆማ ስለነበር፤ ከትጥቅ አምራች ኩባንያዎች (አዲዳስ ወይም ናይክ..) ትጥቅ የሚመጣውና ለሁሉም ስፖርት ፌዴሬሽኖች የሚከፋፈለው በኦሎምፒክ ኮሚቴ በኩል ነው። ለምሳሌ ናይክ ከሆነ ከአምራቹ ጋር ከኦሎምፒክ ኮሚቴው የተወከሉ ሰዎች ሄደው ካምፓኒውን ያናግራሉ። ሯጮች፣ ኳስ ተጨዋቾችና ሌሎች የብ/ቡድን ስፖርተኞች በየፌዴሬሽናቸው በኩል ትጥቁን ተረክበው በኢንተርናሽናል ውድድር የግድ ለብሰው ይቀርባሉ። ጉዱ ያለው ወዲህ ነው፤ ከአምራቹ ጋር ለመነጋገርና ለመሄድ ከፍተኛ ትንቅንቅ አለ። በሻንጣ ዶላር ስለሚዛቅበት። አምራቾቹ ስለሚፎካከሩ ..የግድ የራሳቸውን ምርት በተለይ በአትሌቶቻችን ተለብሶ አለም እንዲያየው ስለሚፈልጉ የግድ ዳጎስ ያለ ዶላር ዝቀው ማጉረስ አለባቸው። ያቺን ነው ሬድዋን የሰሙት። ትጥቅ ለየፌዴሬሽኑ የሚያከፋፍለውን ምስኪን ተቀጣሪ ወጣት ቢጤ ይጠሩና ትጥቅ እንዴት ነው የምታከፋፍለው?..ከስፖርተኞች ተመላሽ የሚሆነው የት ታደርገዋለህ?..ይሉና ያፋጡታል። ወጣቱ ምንም የማይፈራ ደፋር ነው አሉ። ለየፌዴሬሽኑ አስፈርሞ እንደሚሰጥ ይናገርና አክሎም ” ተመላሹን ለራሴ ቅያሪ አልወስደው። የሚጣልበት ስቶር ውስጥ ይገባል” ይላል። ” እንዲህ እያደረጋችሁ ነው ገንዘብ የምትበሉት” ይሉና ሬድዋን በዛው እለት ከስራው ያባሩታል። ሌሎች ተገርመው “አህያውን ፈርቶ..” ብለው አፌዙባቸው። አሁን አሜሪካ የተመደቡት ብርሃነ ኪዳነማርያም ዋናው ዶላር ዛቂ ነበሩ። ያቺ ቦታ ከፍተኛ ሙስና ስላላትና ድምፅ አጥፍቶ ከውጭ አምራች ኩባንያዎች የሚዛቅባት በመሆኑ የመንግስት ባለስልጣናት ይፈራረቁባታል። ሬድዋን እነሱን መድፈር ሲያቅተው ግንኙነት የሌለው ግለሰብ ላይ ክንዱን አሳየ። ብዙም ሳይቆይ ሬድዋን ሲነሳ ወጣቱ ወደስራው ተመለሰ።

እየሩሳሌም አራአያImage result for ሬድዋን ሁሴን

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: