13 የሃይማኖት አባቶች አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቀሉ

በዋልድባ ገዳም እና በተለያዩ ቤተክርስቲያኖች ሲያገለግሉ የነበሩ 13ቱ አባቶች ወደ በረሃ ለመውረድ የወሰኑት አገዛዙ በህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ግፍ እያዩ ዝም ለማለት ህሊናቸውና ሃይማኖታቸው ስላልፈቀደ መሆኑን ተናግረዋል።

ይሄ ጉዳይ የእነ ዶ/ር ብርሃኑ ጉዳይ ብቻ አይደለም ያሉት የሃይማኖት አባቶች የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቅሎ እንዲታገል ጥሪ አስተላልፈዋል፣ ካህናቱ በአማራ ክልል ሕወሃት እየወሰደ ባለው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ መማረራቸውን ገልጸዋል።

የሃይማኖት አባቶቹ ከነ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋና ከሌሎች የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች ጋር እየተነጋገሩ ሕዝቡን እያስተባበሩ እንደሆነ ገልጸዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ በደቡብ ኢትዮጵያ በፓርቲ መሪዎች፣ በፓርቲ አባላት እና በህዝብ ላይ ወታደራዊ የኃይል እርምጃን ጨምሮ ከፍተኛ የሰብዐዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

የገዥው መንግስት በባህር ዳር ከተማ የሚገኙ የብአዴን አባላትን በየክፍለ ከተማው ሰብስቦ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዙሪያና በተከሰቱት ህዝባዊ ተቃውሞዎች ዙሪያ ሰሞኑን ባነጋገረበት ጊዜ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሰበብ የታሰሩት ነጋዴዎችን ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ አባላቱ ጠይቀዋል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: