የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ከሕወሃት ሰራዊት ጋር ከፍተኛ ውጊያ ሲያደርጉ ውለው ከርሰሌት በምትባል ቦታ የሚገኘውን የአደባይ ተራራን ተቆጣጥረዋል።

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ከሕወሃት ሰራዊት ጋር ከፍተኛ ውጊያ ሲያደርጉ ውለው ከርሰሌት በምትባል ቦታ የሚገኘውን የአደባይ ተራራን ተቆጣጥረዋል።

በአሁኑ ወቅት በአርበኞች ግንቦት 7 ሃይሎች እና በሕወሃት ሰራዊት መካከል በቃፍታ ሁመራ አካባቢ ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን ኢሳት በስፍራው የሚገኙ እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል። “የአርበኞች ግንቦት7 የሰሜን ጎንደር አስተባባሪዎች ንቅናቄው ለአንድ ሳምንት በተለያዩ አካባቢዎች ጥቃት ሲፈጽም መቆየቱን እንዲሁም ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ በተለያዩ አካባቢዎች እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ዝርዝር ዘገባውን በምሽት ዝግጅት ይዘን እንቀርባለን።” ኢሳት። ይህ በዚህ እንዳለ ቀደም ብሎ ተመሳሳይ ዜና መቀመጫቸውን በውጭ ሃገራት ባደረጉ አክቲቪስቶች ድርጊቱን “ከፋኝ” የሚባል ሃይል ፈጽሞታል የሚል መረጃ በማኅበራዊ ድረገጾች ተሰራጭቷል። “ከፋኝ” ከረጅም አመታት በፊት በሰሜን ኢትዮጵያ ይንቀሳቀስ የነበረ ሃይል ሲሆን የድርጅቱ መስራቾች ከሌሎች ግንባሮች ጋር ተጣምረው “የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን” እንደመሰረቱ ይታወቃል። “የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር” ከጥቂት አመታት በፊት በፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከሚመራው “ግንቦት 7” ጋር ውሕደት በመፈጸም “አርበኞች ግንቦት 7” እንዲወለድ ምክንያት ሆኗል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: