የባሕርዳር ከተማ የፓርላማ ተወካይን ወ/ሮ አዲሴን ማን ገደላቸው?

ትናንት ከቢሯቸው እንደተገደሉ መረጃዎች ቢወጡም እስካሁን ይህንን ሊያረጋግጥ ወይም ሊያጣጥል የሚችል ማስረጃ አልተገኘም።

ክብርት ወ/ሮ አዲሴ ዘለቀ በ1961 ዓ.ም በደብረማርቆስ ከተማ በተወለዱ ሲሆን ከ1ኛ እስከ 2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ ዘመን ከተማ ተከታትለዋል፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በማኔጅመንት ትምህርት ያገኙ ሲሆን 2ኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በዚሁ ዩኒቨርሲቲ በኤክስኪዩኒቭ ቢዝነስ ማኔጅመንት በ2008 ዓ.ም ማግኘት ችለዋል፡፡

ክብርት ወ/ሮ አዲሴ ዘለቀ በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በባለሙያነትና በኃላፊነት አገልግለዋል፡፡ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከህልፈተ ህይወታቸው ድረስ የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄን (ብአዴን)በመወከል የባህርዳር ከተማ ህዝብ ተመራጭ ሁነው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆን እየሰሩ ነበር፡፡
ትናንት ህዳር 06/2009 በተወለዱ በ48 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም የተለዩት ክብርት ወ/ሮ አዲስ ዘለቀ የሁለት ልጆች እናት ነበሩ፡፡

የቀብር ስነ-ስርዓታቸው በባህር ዳር ከተማ ድንባቄ መድሐኒዓለም ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል፡፡

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: