በጎንደር የነጻነት ትግሉ ፍም እየጣለ ነው

በትናንትናው እለት የነጻነት ትግል ተሳታፊ ናችሁ የተባሉ እስረኞችን ወቅን ከተባለች ስፍራ ወደ ዳባት ከተማ ይዘው በመጓዝ ላይ በነበሩ ፖሊሶች ላይ ሳይታሰብ ድንገት በተከፈተ ተኩስ ሁለት ፖሊሶች ሲገደሉ ሁለት እሰረኞችም በተመሳሳይ ሁኔታ ሰማዕታት ሆነዋል። ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቀ ከፖሊስምሆነ ከእስረኞቹም የቆሰሉ መሆኑ ታውቋል።
የሟቾቹ አስከሬን በዳባት ፖሊስ ጣቢያ በአሁኑ ስአት የሚገኝ ሲሆን ። ዳባት ከተማ ከፍተኛ አለመረጋጋት እና ውጥረት መኖሩ ተረጋግጧል።
ልዩ ስሟ “አንቃሽ “በተባለች ቦታ የነጻነት ኃይሉ ከወያኔ ወንበዴ ሰራዊት ጋር ከፍተኛ ውጊያ በማድረግ ታሪክ የማይረሳው ድል መጎናፀፉ ይታወቃል።
እዚያው የነበሩ የአይን እማኝ ሲናገሩ ” በመሳሪያ ብዛት ፣ በጥራት የማይመጣጠነው የነጻነት ፈላጊው ህዝብ እና መንግስት ነኝ ከሚለው ወንበዴ ጋር የሚደረገው ፍልሚያ በህዝብ በአሼናፊነት መደምደሙ እንደ አድዋ ጦርነት እግዚአብሔር ተዋጊ ሰራዊቱን ልኮ ህዝቡን አግዟል ከማለት ውጭ ሌላ አሳማኝ ቃል የለኝም “ብለዋል

እውነት ነው! በጎንደር የነደደው እሳት ፍም እየጣለ፣ ወያኔ ከገመተው በላይ መቋቋም ከማይችለው ጦርነት ውስጥ ገብቶ እየዋኜ ነው።
በተያያዘ ዜና ከአውሮፖ፣አሜሪካ እና ኢስራኤል ተጉዘው ህዝባቸውን የሚያግዙ ጄግኖች ቁጥርም እየጨመረ ነው።
ይህ መራራ ትግል ዳር እንዲደርስ መላው ኢትዮጵያዊ ይህን ስርአት በመገርሰሱ ተግባር የአቅሙን እገዛ በያለበት ሊያደርግ እንደሚገባ የጎንደር የነጻነት ኃይሎች አደራ ይላሉ።

በተያያዘ ዜና

በበለሳ ግንባር የነጻነት ኃይሉ ከወያኔ ሰራዊት ጋር እየተፋለመ ሲሆን ሰድስት የወያኔ ወታደሮች ልዩ ስሟ “መረብ ” በተባለች ስፍራ መገደላቸው ታውቋል። በርካታ ቁጥር ያላቸው ወተ ታደሮችን ወደ ስፍራው ወያኔ እያጓጓዘም ቢሆን አንድም ቀን አሸናፊ ሳይሆን አስከሬን ተሸካሚ በመሆን ወርደት መከናነቡን በቦታው የሚገኙ የነጻነት ኃይሎች አክለው ገልፀዋል።
ልያ ፋንታጀግና

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: