የሳሞራና የጌታቸው ግብግብ እና እንድምታው

በአሁኑ ሰዓት የህወሓት አገዛዝ የገባበት ቀውስ እየተወሳሰበ ነው። አሁን እውነተኛ የመንግሥት ስልጣን ያለው በሳሞራ የኑስ እጅ ውስጥ ቢሆንም እንኳን ተቀናቃኙ ጌታቸው አሰፋ ሽንፈቱን ሙሉ በሙሉ አልተቀበለም። የሳሞራ የኑስ ቀኝ እጅ የሆነው በገብሬ አድሀና (ዲላ) የሚመራው ወታደራዊ መረጃ የጌታቸው አሰፋን “የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትን” ሊውጥ አፉን ከፍቷል። ጌታቸው የኃይለማርያምን ካቢኔ ከቀውስ የመውጫ ቀዳዳ ሊያደርገው እየጣረ ነው። ጌታቸው የደብረጽዮንን (ግኑኝነታቸው ሞቅ፣ ቀዝቀዝ የሚል ቢሆንም)፣ የወርቅነህ ገበየሁንና የሲራጅ ፈርጌሳን ድጋፍ ያገኛል።

[በነገራችን ላይ የኃይለማርያም አዲሱ ካቢኔን “ጉልቻ ቢለወጥ …” ተተርቶበት የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም። የጌታቸው አሰፋ ቀኝ እጅ የሆነው ወርቅነህ ገበየው ወደ ውጭ ጉዳይ መምጣት እና የገብሬ ዲላ የውጭውን መረጃ ለመቆጣጠር መሞከር የፍልሚያው ሜዳ አገር ውስጥ ብቻ እንዳልሆነ አመላካች ነው። ይህ የአካዳሚ ማዕረጎችን አይቶ ከዚህም ከዚያም የተሰበሰበ “የቀውስ አስወጋጅ” ካቢኔ ቀውስን ማስወገድ ቀርቶ እንደ ቡድን (team) መሥራት መቻሉ እጅግ በጣም አጠራጣሪ ነው። የኃይለማርያም ካቢኔ ጠላት ራሱ ካቢኔው ነው፤ ይህንን ደግሞ እድሜ ካገኘ በጥቂት ወራት ውስጥ የምናየው ይሆናል።]

ሳሞራና ገብሬ ከፍተኛ የብቃት ጉድለት ያለባቸው፤ ሁሉንም ነገር ጉልበት ይገዛዋል ብለው የሚያምኑ፤ የሌላቸው ጉልበት ያላቸው የሚመስላቸው ግብዞች ናቸው። ሳሞራና ገብሬ አገሪቱን ለመቆጣጠር የሚሞክሩት “በኮማንድ ፓስቶቻቸው” በኩል ነው። ልክ እንደመሪያቸው ገብሬ ዲላ የወታደራዊ መረጃ “ኤክስፐርቶች” የኢንተለጀንስ ጥበብን ሀ ሁ የማያውቁ መሀይማን ናቸው። ራሳቸውን “ሁሉን አውቄ” አድርገው ስለሚወስዱ ለመማርም ሆነ ምክር ለመስማት ፈቃደኞች አይደሉም። ገብሬ ዲላ በጌታቸው ሰዎች ከመጠቀም ሰላዮችን ከዩክሬንና ቤላሩስ ቢቀጥር ይመርጣል። የገብሬና የጌታቸው መፋጠጥ የኃይለማርያምን አዲሱን ካቢኔ ከመነሻው ሽባ አድርጎታል። የሳሞራ ሰዎች በየቦታው የልብ ልብ እየተሰማቸው ነው፤ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ደግሞ አባላቱ ቢገፉትም ነቅነቅ አልል ያለው አባይ ወልዱ ነው።

ከዚህ ግብግብ ለትግል ስልት ጥናት የሚጠቅሙን ድምዳሜዎች ምንድናቸው?

1. የኃይለማርያም ካቢኔ ሳይነሳ የተሽመደመደ ነው፣
2. የጌታቸው አሰፋ ሰላዮችና ጆሮጠቢዎች አደጋ ውስጥ ናቸው፤ ራሳቸውን ለማዳን የሕዝብን ትግል መደገፍ ይኖርባቸዋል፣
3. የነፃነት ትግሉ ትኩረት ሳሞራና ገብሬ ዲላ እና እነሱ የሚመሯቸው ተቋማት ላይ መሆን ይኖርበታል። በግልጽ ቋንቋ የትግሉ ቀዳሚ ዒላማዎች በየደረጃው ያሉ ኮማንድ ፖስቶች ሊሆኑ ይገባል፣
4. ግብዞቹ ሳሞራና ገብሬ መንፈቅለ መንግሥት ሊያስቡ እንደሚችሉ ለኃይለማርያምና ካቢኔው እነሆ ሹክ ብለናል።

Bilderesultat for samora yenus

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: