የአየለ ጫሚሶ ቢሮውን አከራይቶ እየበላ ነው “ተባለ

የአየለ ጫሚሶ ቢሮ አራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት ትገኛለች ።በፋይዚት ተከፋፍላ ኮምፒውተር ተደርድሮባት ሁልጊዜም በሯ ወለል ተደርጎ ይከፈታል ።
በሯ ላይ የተለጠፈውን “ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ “የሚል ታፔላ ተመልክተው ወደ ውስጥ ሲያማትሩ ወጣገባ የሚሉ ሰዎችን ይመለከቱና “እንዴ ይሄ ፓርቲ ዘንድሮም ሰው ይከተለዋል “ሊሉ ይችላሉ ።ነገሩ ግን ሌላ ነው ።
የፓርቲው ቢሮ በፋይዚት መከፋፈሉን ነግሬዎት የለ?በክፍልፋዩ አንደኛው ክፍል ለግላጋ ወጣት ተቀምጣ የኮምፒውተር ቁልፎችን እየተጫነች ትቀጠቅጣለች ።ፓርቲው የሚያሰራጨውን ፅሁፍ ከመሰልዎትም ተሸውደዋል ።ልጅቱ የፓርቲው ተከራይ ናት ።
አጠገቧ ፍርድ ቤት በመኖሩ ባለጉዳዮች ሲመጡ እየተቀበለች አቤቱታቸውን ትፅፍላቸዋለች ።ከእርሷ አጠገብ ደግሞ ጠበቃ ይገኛሉ ።እርሳቸውም የፓርቲው ተከራይ ናቸው ።
አየለና ጓደኞቻቸው ወደ ቢሯቸው ብቅ የሚሉት በወር መጨረሻ የቤት ኪራይ ለመቀበል ብቻ ነው ።
እነ አየለን ቢሮው አካባቢ ደጋግመው መመልከት ከጀመሩም በእርግጠኝነት ምርጫ ደርሷል ማለት ነው ።
አሁን አየለና የጥቅም ተጋሪዎቹ ተጋጭተዋል እናም አዲስ አድማስ ቢሮ ሄደው “አየለ ቢሮውን አከራይቶ እየበላ ነው “በማለት ተናግረዋል ።
እውነታው ግን ቢሮዋ መከራየት ከጀመረች አስር ዓመታት መቆጠሩ ነው ።እነዚህ ሰዎች ይህን ሁሉ ጊዜ የት ነበሩ ?

 
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: