የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሃላፊ በኢትዮጵያ የታወጀው የአስቸኳይ ጌዜ አዋጅ እንዳሳሰባቸው ገለፁ

በኦሮሞና አማራ ክልሎች የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አሳስቦኛል ስትል ኖርዌይ ስጋቷል ገለጸች። የአውሮፓ አጋር የሆነችው ኢትዮጵያ በፖለቲካ አለመረጋጋት ስትሰቃይ ማየት በጣም ያሳስባል በማለት የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሃላፊ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ፈጣን የፖለቲካ ማሻሻያ ሳይውል ሳያድር መውሰድ ይኖርበታል ያሉት የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሃላፊ ቦርግ ብሬንዴ (Borge Brende) ፣ በአገሪቷ ያለውን የፖለቲካ ሁኔታም መንግስታቸው በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነ ለጋዜጠኞች አስረድተዋል። በዚህ አስቸጋሪ ወቅት አጋራችን ኢትዮጵያን ጋር ሰላም በሚሰፍንበት ሁኔታ ላይ መነጋገራችንን መቀጠል እፈልጋለሁ ሲሉ ተናገረዋል።

ሚስተር Brende በአገሪቷ የተቀሰቀሰው አለመረጋጋትና ያንን ተከትሎ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እጅግ አሳስቦኛል ካሉ በኋላ፣ ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ እንዳይወጣ በትብብር መስራት ያስፈልጋል ሲሉም አስረድተዋል። ከኢትዮጵያ ህዝብ ግማሹ ወይም 50 ሚሊዮን የሚሆኑ ወጣቶች ስራ በመፈለግ የተሰማሩ፣ የመናገር ነጻነት እንዲከበርላቸው የሚፈልጉ እና በአገሪቷ የፖለቲካ ሂደት ተሳትፎ ማድረግ የሚፈልጉ መሆናቸውን ሚስተር ብሬንድ አስረድተዋል።

ካለፈው ሳምንት ማክሰኞ ጀምሮ የምስራቅ አፍሪካን የጎበኙት ሚስተር ብሬንድ የደቡብ ሱዳን፣ የኬንያ፣ የሶማሊያና ኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናንት ማነጋገራቸው ታውቋል። ኢትዮጵያን በጎበኙ ጊዜም አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንዳነጋገሯቸው ታውቋል።

Image result for Borge Brende

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: