ሰበር መረጃ . . በደቡብ አፍሪካ ህወሃት በድጋሚ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ደግፉልኝ ስብሰባ ጠራ!

በቅርቡ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ የደነገገዉ ህወሃት በመላዉ አለም በሚገኙ ተቃዋሚዎች ላይ ተጽእኖ ለማሳደር በኢንባሲዎች አማካኝነት የስብሰባና የተቃዉሞ ሰልፍ በደጋፊዎቹ አማካኝነት ሊያደርግ እንደነበር መጠቆማችን የቅርብ ግዜ ትዉስታ ነዉ። በመሆኑም ህወሃት የመጀመሪያዉን ስብሰባ በደቡብ አፍሪካ ፍሪ እስተት ሊያደርግ ዝግጅቱን ጨርሶ በነበረት ወቅት መረጃዉ ቀድሞ በመዉጣቱ ምክንያት ዉድ የኢትዮጵያ ልጆች በግንባር ስፍራዉ ድረስ በመሄድ በዚህ እኩይ ተግባር ላይ የተሳተፉ ግለሰቦችን በማነጋገር ከዚህ አስነዋሪ ተግባር እራሳቸዉን እንዲያገሉ በማድረጋቸዉ የወያኔ ተንኮላዊ ሴራ ከሽፏል። ነገር ግን በቃኝ የማይለዉና ሽንፈቱን የምይቀበልዉ የህዝብ ተላት የሆነዉ የጎጥ ቡድን አሁንም በድጋሚ በ30/10/2016 ፕሪቶሪያ እስኩማን እስትሬት በሚገኘዉ ኢንባሲዉ ዉስጥ በዚሁ በመከረኛዉ እና በከሸፈዉ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ምክንያት እንነጋገር እያለ እትዮጵያዊያንን እያስጨነቀ እንደሚገኝ ከስፍራዉ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ተወካዩ የህወሃት ኢንባሲ በሊስቱ ዉስጥ የመዘገባቸዉን ወገኖቻችንን በተለይም የስርአቱ ደጋፊዎች እና ሐገር ቤት ሀብት ንብረት ያፈሩ እንዲሁም ከኢናባሲዉ ጋር በተገናኘ መልኩ አንዳንድ ቁልፍ የቤተሰብና የግል ጉዳይ ያላቸዉ ግለሰቦች ጋር እየደወለ በስብሰባዉ ላይ ካልተገኛችሁ ” በስቸክዋይ ግዜ አዋጁ አፈጻጸም ላይ ትብብር አለማድረጋችሁንና ከህዝብ ጋር አለመቆማችሁን በመገንዘብ ሚናችሁን ለሚመለከተዉ አካል ኢናስተላልፋለን ” በማለት እያስፈራራ እንደሚገኝ ከኢንባሲዉ ዉስጥ እና በደቡብ አፍሪካ መሐበረሰብ ዉስጥ ከሚኖሩ ወገኖቻችን የደረሰን መረጃ ጠቁሟዋል። ዉድና የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ይህ የህዝብ ጠላት የሆነዉ ስርአት በሀገር ቤት በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ የፈጸመዉንና እየፈጸመ የሚገኙዉን አፈና ደግፉልኝ እንዲሁም ከሀገራቸዉ ተሰደዉ ስለ ነጻነታቸዉ እና ስለመብታቸዉ የሚጮሁትን ስደተኞች ተቃወሙልኝ በማለት የጠራዉ ስብሰባ ላይ ባገኘት ብቻ ሳይሆን ስብሰባዉን በመቃወም የበኩላችሁን አስተዋጾ ኢንድትወጡ እናሳስባለን። ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: