“ህወሃት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በኢህአዴግና በመንግስት ላይ መፈንቅለ መንግስት አድርጓል”ጠበቃ ተማም አባቡልጉ

“ህወሃት በሌሎች የኢህአዴግ አባልና አጋር ድርጅቶች፣ ራሱ የፈጠራቸው የይስሙላ የፌዴራልና የክልል መንግስታት መዋቅሮች ላይ መፈንቅለ መንግስት አድርጎ፣ ቀድሞ ያዙልኝ ሲል ለእነዚህ ሰጥቶ የነበረውን ስልጣን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስም መልሶ የተቀበለበት፣ የራሱን እጅ ስራ የሆኑትን መስተዳድሮችና መዋቅሮችን የገለበጠበት ድርጊት ነው። ከጉልበት ሌላ አስመስሎ የመግዛት አቅም ስለሌለውም እነ ኦህዴድ ባይኖሩ ኖሮ ህወሃት፣ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያውጅ የነበረው በ1984 ዓ.ም ነበር። አሁን የህወሃት ትግል ወደ ሁለተኛ ደረጃ (phase) ተሸጋገሯል። ይህም ህወሃት ከጀርባ ሆኖ አንዳንዴ ብቅ እያለ ከአባልና አጋር ድርጅቶች አቅም በላይ የሆኑ ሁኔታዎችን ተቆጣጥሮና አረጋግጦ ለእነሱ በመመለስ ወደመጋረጃ ጀርባ ከሚመለስበት ሁኔታ ወጥቶ፤ ሁሌም እሱ ፊት ለፊት ሆኖ ከእነሙሉ ጉልበቱ ከህዝብ ጋር ወደሚፋጠጥበት ሁለተኛውና ዋናው ትግል መግባታቸውን የሚያሳይበት ነው። ይህንን ትግል (አሁን) የሚያሸንፈው በእርግጥም የኢትዮጵያ ባለቤት ይሆናል። ህወሃት ዳግም በአባልና አጋር ድርጅቶች አማካኝነት ኢትዮጵያን ወደመግዛት መመለስ ከቻለ የኢትዮጵያ ህዝብ ተሸነፈ ማለት ይሆናል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በህዝቡ ትግል የተነቃነቀውንና አደጋ ላይ የወደቀውን፣ ህወሃት በትግሌ አገኘሁት የሚለውን ኢትዮጵያን ቅኝ የመግዛት ፍጹማዊ ስልጣኑን ወደነበረበት ለመመለስ የሚያደርገውን መልሶ የማጥቃት እርምጃ የዳቦ ስም ነው። ስለዚህ ህዝቡ በብስለት ማድረግ ያለበትን ማድረግ አለበት።”

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to “ህወሃት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በኢህአዴግና በመንግስት ላይ መፈንቅለ መንግስት አድርጓል”ጠበቃ ተማም አባቡልጉ

  1. በለው! says:

    —- የተፃፈውን” የዘገምተኛ ግዜ እወጃ” በተለያዩ የፖለቲካ ተንታኝኞች በተለያየ ድረ ገፅና ማውሪያ መንገድ ሁሉ ደጋግመው ሲያወሩ ሲያደንቁ ሲዘባነኑ የአዋጁ የስራ ግዜ አልቆ የሚሰብሩበትን ሰብረው፡ የገድሉትን ተስካር በልተው፡ ጨርሰዋል።
    — **** ” ህወሓት ሁሌም እሱ ፊት ለፊት ሆኖ ከእነሙሉ ጉልበቱ ከህዝብ ጋር ወደሚፋጠጥበት ሁለተኛውና ዋናው ትግል መግባታቸውን የሚያሳይበት ነው። ይህንን ትግል (አሁን) የሚያሸንፈው በእርግጥም የኢትዮጵያ ባለቤት ይሆናል። ”
    *** “ህወሃት ዳግም በአባልና አጋር ድርጅቶች አማካኝነት ኢትዮጵያን ወደመግዛት መመለስ ከቻለ የኢትዮጵያ ህዝብ ተሸነፈ ማለት ይሆናል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በህዝቡ ትግል የተነቃነቀውንና አደጋ ላይ የወደቀውን፣ ህወሃት በትግሌ አገኘሁት የሚለውን ኢትዮጵያን ቅኝ የመግዛት ፍጹማዊ ስልጣኑን ወደነበረበት ለመመለስ የሚያደርገውን መልሶ የማጥቃት እርምጃ የዳቦ ስም ነው። ስለዚህ ህዝቡ በብስለት ማድረግ ያለበትን ማድረግ አለበት።”

    Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: