በህወሀትና ብአዴን መካከል የተፈጠረው ፓለቲካዊ ፍጥጫ

የብአዴን ስብሰባ ዛሬም ቀጥሏል።

 አማራ ያልሆኑትን እነዚህ ከፊት ለፊት የሚያታዩትን ካሳ ተ/ብርሀን፣ከበደ ጫኔን፣ሴኩ ቱሬ፣ፍሬህይወት፣ በረከት፣….እና የመሳሰሉ የያዘው ብአዴን ካለፈው አመት ጀምሮ የእነዚህን የህወሀት መልዕክተኞች ዱላ ለመቋቋም በመሞከሩ ከህወሃት በኩል ብአዴን የነፍጠኛ ስርዓትን ለመመለስ እየታገለ ነው የሚል የአደባባይ ወቀሳ ደርሶበታል።
በአዴን ውስጥ ሁለት ቡድን አለ የትግራይ ነፃ አውጭ ቡድንን የሚደግፈው የእነ ካሳ እና ከበደ ጫኔ ቡድንና የአማራ ለአማራ የሚለው የእነ ገዱ እና 80 በመቶ የክልል፣የዞንና የወረዳ አመራራ የሚደግፈው የአዲሱ ትውልድ አስተሳሰብ።ይህንን ቡድን ወጣ ገባ እያሉ የሚደግፉ የእነ ደመቀ እና አለምነው አይነት ሰዎችም አልፎ አልፎ እንደሚደግፉት ይነገራል።

በስበሀት ነጋ የሚሽከረከረው ህወሀት የብአዴን አመራር ገዱ አንዳርጋቸውና ተከታዮቹ ከክልሉና ከፖርቲው ሊባረሩ ይገባል..የሚለው በነበረከት ቡድን ተቀባይነት ባለማግኘቱ ፍጥጫው መክረሩን ያመለከቱት ምንጮች ብአዴን ይህን አቋም ሊወስድ የቻለው የትግራይ ክልል ፕ/ት አባይ ወልዱ ከክልሉ ተነስተው አዲስ ይዋቀራል በተባለው ካቢኔ በሚኒስትር ስልጣን ሊቀመጡ መታቀዱን መረጃው ስለደረሳቸው ነው ብለዋል። “አባይ ወልዱን ከስልጣን ስታነሱ እኛም ገዱን እናነሳለን” የሚል መደራደሪያ አቅርበው የነበሩት ብአዴን በመጨረሻ አባይ ለተሻለ ስልጣን መታጨታቸውን መረጃ ሲያገኙ ገዱንና ተከታዮቻቸውን በማስጠንቀቂያ እንዳለፏቸው በመግለፅ አቋም መያዛቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል።

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: