የወያኔ መንግስት የአሜሪካን መግለጫ አጣጣለው

የአሜሪካ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አስመልክቶ ያወጣውን መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት አጣጥለውታል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት አፈ ቀላጤ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ መግለጫውን ‹‹የኢትዮጵያን መረጋጋት እና ሰላም ከማይመኙ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ጥቂት ሰራተኞች የተሰጠ መግለጫ ነው፡፡›› ሲሉ ተችተውታል፡፡ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ላይ፣ አስቸኳይ አዋጁ የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ ተገቢውን ስራ እንዳያከናውን ማነቆ እንደሆነበት መግለጹ ይታወቃል፡፡
የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር የሆኑት አቶ ጌታቸው ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የእንግሊዝኛው አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ሀገሪቱ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በኋላ መረጋጋት እና ሰላም እንደሰፈነባት የገለጹ ሲሆን፣ ሀገሪቱ ለመረጋጋቷ ማስረጃው ምንድነው ተብለው ጥያቄ ቢቀርብላቸውም ተጨባጭ ማስረጃ መስጠት ሳይችሉ ቀርተዋል-አቶ ጌታቸው ረዳ፡፡
ሀገሪቱ ተረጋግታለች መባሉን ተከትሎ ጥያቄ የቀረበላቸው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀ መንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ‹‹ሀገሪቱ አሁንም መስቀለኛ መንገድ ላይ ነች›› ብለዋል፡፡ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች መንግስት ያሰማራቸው ወታደሮች ሴት እየደፈሩ፣ እየዘረፉ፣ እና ሰዎችን እየገደሉ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር መረራ፣ ‹‹ይሔ ነው መረጋጋት ማለት?›› ሲሉ በአግራሞት ጠይቀዋል፡፡ አባሎቻቸው ከተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች እየታደኑ እንደሚታሰሩም ዶክተሩ ተናግረዋል፡፡ በምሳሌነትም ከምዕራብ አርሲ አሚዶ አቡ፣ ከአርሲ አህመድ መሐመድ፣ ከባሌ መሐመድ አሊ እና ሌሎችም የኦፌኮ አባላት መታሰራቸውን ዶ/ር መረራ ገልጸዋል፡፡ ይህም ሀገሪቱ ወደ ባሰ ሁኔታ እያመራች መሆኗን እንጂ እየተረጋጋች መሆኗን አያመላትም ብለዋል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ የሽዋስ አሰፋ በበኩላቸው ከገዥው ፓርቲ ሀገሪቱ እየተረጋጋች ነው ተብሎ የተሰጠውን መግለጫ አብጠልጥለውታል፡፡ ‹‹ሀገሪቱ ተረጋጋች ከተባለ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለምን አይነሳም ታዲያ?›› ሲሉ የጠየቁት አቶ የሸዋስ፣ በአማራም ሆነ በኦሮሚያ መረጋጋት የሚባል ነገር እንደሌለ ገልጸዋል፡፡ ‹‹የህዝብ ጥያቄ የስርዓት ለውጥ ነው›› ያሉት አቶ የሽዋስ፣ ሰዎች በገዛ ፈቃዳቸው መሳሪያቸውን አስረክበው እጃቸውን ለመንግስት እየሰጡ ነው ተብሎ በገዥው ፓርቲ የሚወራውን ወሬ ‹‹ድራማ ነው›› ሲሉ አጣጥለውታል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጎቹ ወደ አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች እንዳይሔዱ አስጠንቅቋል፡፡ እጅግ አንገብጋቢ ጉዳይ ካልሆነ በቀር ዜጎቹ ወደ ኦሮሚያም ሆነ አማራ ክልሎች እንዳይጓዙ ያስጠነቀቀው የብሪታንያ መንግስት፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ምዕራብ እና ሰሜን እንዲሁም ደቡባዊ ምዕራብ ሸዋ ወደተባሉት የኦሮሚያ ስፍራዎች መጓዝ አደገኛ መሆኑን ጠቅሷል፡፡
18593_888840351183833_4627943239101949574_n

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: