የብሪታኒያ መንግስት የሃገሪቱ ዜጎች አስቸኳይ ከሆነ ተልዕኮ ውጭ ወደ አማራና የተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች እንዳይጓዙ አሳሰበ

በኢትዮጵያ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ የብሪታኒያ መንግስት የሃገሪቱ ዜጎች አስቸኳይ ከሆነ ተልዕኮ ውጭ ወደ አማራና የተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች እንዳይጓዙ አሳሰበ።
በዚሁ አዋጅ መውጣት ዙሪያ ስጋቷን ስትገልፅ የቆየችው አሜሪካ ከቀናት በፊት ዜጎቿ ተመሳሳይ ማሳሰቢያን ማሰራጨቷ ይታወሳል።
በኢትዮጵያ ስላለው የፖለቲካ ጉዳይ ሪፖርን ያወጣው የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጎቿ ሙሉ ለሙሉ እጅግ አስቸኳይ ከሆነ ተልዕኮ ውጭ ጉዳይ አማራ ክልል እንዳይጓዙ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።
በኦሮሚያ ክልል ዳግም በምስራቅ ሸዋ፣ በምዕራብና በሰሜን እንዲሁም በደቡባዊ ምዕራብ የሸዋ ስፍራዎች የብሪታኒያ ዜጎች ጉዞን እንዳያደርጉ ምክርን ተለግሰዋል።
በቅርቡ ተከታታይ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ሲካሄዱባቸው የነበሩ የአርሲና የምዕራብ አርሲ ዞኖች ጉዞ እንዳይደረግባቸው ከተጠቀሱ አካባቢዎች መካከል እንደሚገኙበት የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድጋሚ ባወጣው የጉዞ ማሳሰቢያ መግለጫው አመልክቷል።
ከተጣለው የጉዞ እገዳ በተጨማሪ የብሪታኒያ መንግስት በአዲስ አበባ የሚገኙ ዲፕሎማቶች ከመዲናዋ ውጭ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ የተለመደ ተግባርን እንዳይወጡ አድርጎ እንደሚገኝም ገልጿል።
በሃገሪቱ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘውን የአስቸኳይ ጊዜ ዋጅ ተከትሎ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና የተለያዩ አካላት ድርጊቱ የሰብዓዊ መብትን ጥሰትን ሊያባብስ ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛል።
የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እየወሰዱ ባለው ዕርምጃ ወደ 2ሺ አካባቢ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውን ፖሊስ ቢገልጽም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ቁጥሩ ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችል ይገልጻሉ።

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: