“በረከት ቢሮ ገብቼ እንደፈለግኩ ተሳድቤ እወጣለሁ!” አለ ኮተታሙ ሳምሶን ማሞ

ቁም-ነገሩ “ማንን ነው የምትሳደበው?” ነው። ላንተ የዲሞክራሲ መለኪያው እሱ ከኾነ አራት ኪሎ ቤተ-መንግስት ጋር ቆመህም በጩኸት ፕሬዚዳንቱን መሳደብ ትችላለህ- የግብጽን ወይም የኤርትራን።
አስተውላችሁ ከሆነ ቅቤ መጥበስ በለመደ ምላሱ ልክ እንዲህ እያለ ሲወሳልት ነው መድረክ መሪው “በቃ፣ በቃ” ያለው። ማን እንደኾነ ያውቁታላ። እዚያ ስብሰባ ላይ አስተያዬት ከሰነዘሩት መካከል ፦” በቃ ፣በቃ” ተብሎ እንዲያቆም የተደረገውም እሱ ብቻ ነው። “እንዴት ያፍር?” እንዳንለው፣ ሰውዬው ኃፍረት የሚባል ነገር አልፈጠረበትም።

Image result for samson mamo
ደግሞ አዲስ አቋም ያለው ይመስል ደረቱን ነፍቶ፦“ይሄ ስርዓት እንዲቀጥል እፈልጋለሁ” ይላል።ይህን ሳትነግረን እናውቃለን።ይደንቀን የነበረው ሌባ-የሌባን ሥርዓት እንዳይቀጥል ቢፈልግ ነበር።
ይህን አለና ሰሞኑን በር ዘግተውበታል መሰል እነ ኢቲቪን ዘነጣጠለ። አለቃቸውንና አሠሪያቸውን አቶ በረከትን እያሞገሰ የታችኞቹንና ታዛዦቹን መቦጨቅ ጀመረ። ሲጀምር ሀገራዊ አርበኛ መስሎ የቀረበውም፤ ቲቪ አካባቢ ካለችበት የጥቅም ግጭት በመነሳት ነው። እናም “ቲቪው ላይ እኛን ሹሙን ወይም ጣቢያ እንድናቋቁም ፍቀዱልን” በሚመስል አቤቱታ አቅመ ቢሶቹ ላይ ወረደባቸው።
እነ ኢቲቪን የሚከሰው ሳምሶንኮ የዛሬ አምስት ዓመት አካባቢ መለስ ጋዜጣዊ መግለጫ ሢሰጡ የኢፍቲን እህት የሆነችውን ኢትዮ ቻነል የተስኘት ጋዜጣውን ወክሎ ተገኝቶ ምስኪን የጋዜጣ አዟሪዎችን ከሠስኩ ብሎ ራሳቸውን መለስን ያሸማቀቀ ነው።
“ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ሌላው ቀርቶ የጋዜጣ አዟሪዎች አድመውብናል። ለምንድነው የኛን ጋዜጣ ከስር የምትደብቁት ስንላቸውም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ፎቶ ፊት ለፊት ገጽ ስለምታወጡ ነው። ሰው ገና ፎቶውን ሲያይ ጥሎን ይሄዳል፣ ገዥ አናገኝም ይሉናል፣ አዟሪዎች ሳይቀሩ በአቅማቸው እንዲህ ተጽእኖ እያረጉብን ነው”በማለት ነው ጠየቅኩ ብሎ ያሸማቀቃቸው።
ይህን ሲል እሱ በአዟሪዎች እንጀራ ላይ መቆሙንና ታማኝነቱን መግለጹን እንጂ -አቶ መለስ ምን ይሰማቸዋል? ብሎ እንኳ አላሰበም።
እኔ ሽምቅቅ ልበልለትና ሟቹም ይህን ሀቅ ሢሰማ ፣ ሰው ይህን ያህል እንደጠላው በአፈ ጮሌው አማካይነት መርዶው ሢደርሰው አንገቱን ሲደፋ አስታውሳለሁ።
እንግዲህ እንዲህ እንደ ጋሪ ፈረስ በአንድ አቅጣጫ ብቻ የሚያይ ሰው ነው- “ሚዲያው ቢሰጠን ከውጪ የሚመጣውን ፕሮፓጋንዳ የሚያከሽፍ ብቃት ያለው ሥራ መሥራት እንችላለን” ዐይነት አቤቱታ በዘዴ እያቀረበ ያለው።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: