ሪያድ-ሳውዲው ልዑል አንገቱን ተቀላ፣ ጅዳ – ኢትዮጵያዊው ነጻ ተባለ !

” ኢትዮጵያዊው የገደለው ራሱን ለመከላከል ነውና ነጻ ነው! ”

ሳውዲ አረቢያ የንጉሳውያን ቤተሰብ አባል የሆኑት ልዑል ቱርኪ ቢን ሳዑድ አል ቱርኪ በፈጸሙት የግድያ ወንጀል በተላለፈባቸው ውሳኔ መሰረት በትናንተናው እለት አንገታቸው መቀላቱን የሳውዲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል ። ሳውዲው ልዑል አንገታቸውን የተቀሉት አድል ቢን ሰልማን አብድልከሪም መሀመድ የተባሉ ሳውዲ ዜጋን መግደላቸው በመረጋገጡ መሆኑን መረጃው ያትታል ።: ልዑሉ ግድያውን የፈጸሙት ከሪያድ ወጣ ብሎ በሚገኝ አል ቱማማ al-Thumama በተባለ ስፍራ በተፈጠረ ግጭት መሆኑንም ተጠቁሟል። የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መግለጫ በማከልም የግድያው ወንጅል ከተፈጸመ ጀምሮ በተደረገው ከፍተኛ ማጣራት ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከሶስት አመት በፊት ልዑሉን ጥፋተኛነት አረጋግጧል ። ፍርድ ቤቱ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረትም ጉዳዩ ለከፍተኛ የሳውዲ መንግስት አካላት ቀርቦ ይሁንታ ማግኘቱን ሲታወቅ የሟች አድል ቢን ሰልማን አብድልከሪም መሀመድ ቤተሰቦች ካሳ ቀርቦካቸው ፍርድ ሲፈጸም እንጅ የቀረበላቸውን ካሳ እንደማይቀ በሉ በማሳወቃቸው የልዑሉ አንገት በትናንትናው እለት መቀላቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ሲያስረዳ በንጹሃንን ላይ ወንጄል የሚፈጽ ም ማናቸውም ሰው ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ መግለጫው አስታውቋል ።

ይህ በእንዲህ እዚህ ጅዳ ውስጥ ከሁለት አመት በፊት ፈይሰልያ በተባለ አካባቢ የኢትዮጵያዊውን አባወራ ቤት ለመዝረፍ ሲመክር በተፈጠረ ግብግብ ነፍስ የጠፋው ኢትዮጵያዊ ኑረሁሴን ሀሰን ሙስ ጦፋ ከተከሰሰበት የግድያ ወንጄል ነጻ መሆኑ ታውቋል ። በመኖሪያ ቤቱ አገር ሰላም ብሎ ተቀምጦ እያለ ለዘረፋ ከመጡ ሳውዲ ወጣቶች ጋር ነበር የተጋጨው ። ዘራፊ ወጣቶች እሱን ወንድሞቹንና የቀሩትን ወንዶች በአንድ ክፍል በመዝጋት በቤቱ ያለውን ንብረት ከዘረፉ በኋላ ሚስቱን ሊደፍሩ ሲሞክሩ የተዘጋበትን ቤት ሰብሮ በመውጣት ከሳውዲ ወጣት ጋር ግብግብ የገጠመው ሁሴን ራሱን ለመከላከል ሳውዲው ወጣት ይዞት የነበረውን ስለት በመቀማት ሊገድለው እንደቻለ ለፍርድ ቤት አምኖ ነበር ።

ኢትዮጵያዊው ሁሴንን ከዚህ ቀደም ባቀረብኩት የማለዳ ወግ በሰጠን ቃለ ምልልስ ግድያ የፈጸመው ራሱ ለመከላከል መሆኑን በመግለጽ የሀገሩ መንግስት ተወካዮች ቀርበው ስለመብቱ መከራከር ባይችሉም ጉዳዩን ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱን አጫውቶን ነበር ። ከሳምንታት በፊት ጉዳዩን ለሁለት አመት ተኩል የመረመረው ከፍተኛ የሸሪያ ፍርድ ቤት ሁሴን ግድያውን ራሱን ለመከላከል ሲል መፈጸሙን በመግለጽ ከቀረበበት ወንጀል ነጻ እንዳለው በስልክ ባደረግነው ቃለ ምልልስ ግልጾልኛል ። አቅም ሲገቅድ ዝርዝሩን የጉዳዩ ባለቤት ሁሴን ሀሰን ያጫውቶኛል !

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ
ጥቅምት 2009 ዓም

 

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: